1 ሳሙኤል 8:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከግብፅ ካወጣኋቸው ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን ትተው እንግዶች አማልክትን በማምለካቸው እንደ ሠሩት ሥራ ሁሉ እንዲሁ በአንተ ደግሞ ያደርጉብሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከግብጽ ምድር ካወጣኋቸው ዕለት አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን ትተው ሌሎች አማልክትን በማምለክ ያደረጉትን ሁሉ በአንተም ላይ እያደረጉ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከግብጽ ምድር ካወጣኋቸው ቀን አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን ትተው ሌሎች አማልክትን በማምለክ ያደረጉትን ሁሉ በአንተም ላይ እያደረጉ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እነርሱን ከግብጽ ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ፊታቸውን መልሰው ከእኔ በመራቅ ባዕዳን አማልክትን ሲያመልኩ ኖረዋል፤ እንግዲህ በእኔ ላይ ሲያደርጉት የነበረውን ሁሉ እነሆ በአንተም ላይ መፈጸም ጀምረዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከግብጽ ካወጣኋቸው ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን ትተው እንግዶች አማልክት በማምለካቸው እንደ ሠሩት ሥራ ሁሉ እንዲሁ በአንተ ደግሞ ያደርጉብሃል። |
የእስራኤልም ልጆች አሉአቸው፥ “በሥጋው ምንቸት አጠገብ ተቀምጠን እስክንጠግብ ድረስ እንጀራና ሥጋ በምንበላበት ጊዜ በግብፅ ምድር በእግዚአብሔር እጅ ምነው በሞትን! ይህን ጉባኤ ሁሉ በራብ ልትገድሉ እኛን ወደዚች ምድረ በዳ አምጥታችኋልና።”
ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፥ “የምንጠጣውን ውኃ ስጠን” አሉ። ሙሴም፥ “ለምን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተናላችሁ?” አላቸው።
ሕዝቡም ሙሴ ከተራራው ሳይወርድ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ፥ ወደ አሮን ተሰብስበው፥ “ይህ ከግብፅ ምድር ያወጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ሆነ አናውቅምና ተነሥተህ በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን” አሉት።
ስድስት ዓመት በተፈጸመ ጊዜ፥ የተሸጠላችሁን፥ ስድስትም ዓመት የተገዛላችሁን ዕብራዊ ወንድማችሁን እያንዳንዳችሁ አርነት ታወጡታላችሁ፤ አባቶቻችሁ ግን አልሰሙኝም፤ ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም።
እርሱም እንዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እኔን ወደ አስመረሩኝ ወደ እስራኤል ቤት እልክሃለሁ። እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ድረስ ዐመፁብኝ።
በነጋውም የእስራኤል ልጆች ሁሉ፥ “እናንተ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ገድላችኋል” ብለው በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ።
የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያን እጅ አርባ ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው።
እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ፤ እንዲህም አለ፥ “ይህ ሕዝብ ለአባቶቻቸው ያዘዝሁትን ቃል ኪዳን ስለ ተላለፉ፥ ቃሌንም ስላልሰሙ፥
የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግዚአብሔርም በምድያም እጅ ሰባት ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው።
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን አለው፥ “በእነርሱ ላይ እንዳልነግሥ እኔን ናቁ እንጂ አንተን አልናቁምና በሚሉህ ነገር ሁሉ የሕዝቡን ቃል ስማ።
አሁንም ቃላቸውን ስማ፤ ነገር ግን ጽኑ ምስክር መስክርባቸው፤ በእነርሱም ላይ የሚነግሠውን የንጉሡን ሥርዐት ንገራቸው።”