Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 2:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እኔን ወደ አስ​መ​ረ​ሩኝ ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት እል​ክ​ሃ​ለሁ። እነ​ር​ሱና አባ​ቶ​ቻ​ቸው እስከ ዛሬ ድረስ ዐመ​ፁ​ብኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ በእኔ ላይ ወደ ዐመፀው፣ ወደ ዐመፀኞቹ የእስራኤል ልጆች እልክሃለሁ፤ እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ድረስ ዐምፀውብኛል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ወደ እስራኤል ልጆች፥ ወደ ዓመፀኞች አገር፥ በእኔ ላይ ወደ ዐመፁት እልክሃለሁ። እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ቀን ድረስ በእኔ ላይ ዐመፁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! በእኔ ላይ ወደ ዐመፁት ወደ እስራኤል ሕዝብ እልክሃለሁ፤ እነርሱና የቀድሞ አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ድረስ በእኔ ላይ እንዳመፁ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ በእኔ ላይ ወደ ዐመፁ ወደ ዓመፀኞች ሰዎች ወደ እስራኤል ልጆች እልክሃለሁ። እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ድረስ ዐመፁብኝ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 2:3
42 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ላ​መኑ ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አን​ገት ይልቅ አን​ገ​ታ​ቸ​ውን አደ​ነ​ደኑ እንጂ አል​ሰ​ሙም።


የገ​ባ​ላ​ቸ​ው​ንም ቃል ኪዳን ሁሉ አል​ጠ​በ​ቁም። ከንቱ ነገ​ር​ንም ተከ​ተሉ፤ ከን​ቱም ሆኑ፤ እንደ እነ​ር​ሱም እን​ዳ​ይ​ሠሩ ያዘ​ዛ​ቸ​ውን በዙ​ሪ​ያ​ቸው ያሉ​ትን አሕ​ዛብ ተከ​ተሉ።


ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ዘመን ጀም​ረን እስከ ዛሬ ድረስ እጅግ በድ​ለ​ናል፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን እኛና ልጆ​ቻ​ችን ንጉ​ሦ​ቻ​ችን፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ች​ንም ለሰ​ይ​ፍና ለም​ርኮ፥ ለብ​ዝ​በ​ዛና ለዕ​ፍ​ረት በአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት እጅ ተጣ​ልን፤ እስከ ዛሬም ድረስ በፊ​ታ​ችን እፍ​ረት እን​ኖ​ራ​ለን።


“ነገር ግን ተመ​ል​ሰው ዐመ​ፁ​ብህ፤ ሕግ​ህ​ንም ወደ ኋላ​ቸው ጣሉት፤ ወደ አን​ተም ይመ​ለሱ ዘንድ የመ​ሰ​ከ​ሩ​ባ​ቸ​ውን ነቢ​ያ​ት​ህን ገደሉ፤ እጅ​ግም አስ​ቈ​ጡህ።


በተ​ጨ​ነቁ ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፥ ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው።


ለዐ​መ​ፀ​ኞች ልጆች ወዮ​ላ​ቸው! ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከእኔ ዘንድ ያል​ሆ​ነን ምክር ይመ​ክ​ራሉ፤ ኀጢ​አ​ት​ንም በኀ​ጢ​አት ላይ ይጨ​ምሩ ዘንድ ከመ​ን​ፈሴ ዘንድ ያል​ሆ​ነ​ውን ቃል ኪዳን ያደ​ር​ጋሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እን​ዲህ አለኝ፥ “ወደ​ም​ል​ክህ ሁሉ ዘንድ ትሄ​ዳ​ለ​ህና፥ የማ​ዝ​ዝ​ህ​ንም ሁሉ ትና​ገ​ራ​ለ​ህና፦ ሕፃን ነኝ አት​በል።


ከት​ን​ሽ​ነ​ታ​ችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባ​ቶ​ቻ​ችን በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኀጢ​አት ሠር​ተ​ና​ልና፥ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ን​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ን​ምና በእ​ፍ​ረ​ታ​ችን ተኝ​ተ​ናል፤ ውር​ደ​ታ​ች​ንም ሸፍ​ኖ​ናል።”


“አንድ የመ​ጽ​ሐፍ ክር​ታስ ውሰድ፥ ለአ​ን​ተም ከተ​ና​ገ​ር​ሁ​በት ቀን ከይ​ሁዳ ንጉሥ ከኢ​ዮ​ስ​ያስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ላይ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ህን ቃል ሁሉ ጻፍ​በት።


ኤር​ም​ያ​ስም ይህን ቃል ለመ​ለ​ሱ​ለት ሕዝብ ሁሉ፦ ለወ​ን​ዶ​ቹና ለሴ​ቶቹ፥ ለሕ​ዝ​ቡም ሁሉ መለ​ሰ​ላ​ቸው እን​ዲ​ህም አለ፦


“እና​ን​ተና አባ​ቶ​ቻ​ችሁ፥ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ች​ሁም፥ አለ​ቆ​ቻ​ች​ሁም የም​ድ​ርም ሕዝብ በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ ያጠ​ና​ች​ሁ​ትን ዕጣን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሰ​በው፥ በል​ቡም ያኖ​ረው አይ​ደ​ለ​ምን?


“በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በር ቁም፤ ይህ​ንም ቃል እን​ዲህ ብለህ ተና​ገር፦ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትሰ​ግዱ ዘንድ በእ​ነ​ዚህ በሮች የም​ት​ገቡ ከይ​ሁዳ ያላ​ችሁ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


“የሰው ልጅ ሆይ፥ ለአ​ስ​ቈ​ጡኝ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ይህ ትር​ጓሜ ምን እንደ ሆነ አታ​ው​ቁ​ምን? በላ​ቸው። እን​ዲ​ህም ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ እነሆ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ፤ ንጉ​ሥ​ዋ​ንና መኳ​ን​ን​ቶ​ች​ዋ​ንም ማረከ፤ ወደ ሀገ​ሩም ወደ ባቢ​ሎን ወሰ​ዳ​ቸው።


ለዐ​መ​ፀ​ኛ​ውም ቤት ምሳ​ሌን ተና​ገር እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጣድ፥ ድስ​ቲ​ቱን ጣድ፥ ውኃም ጨም​ር​ባት።


ያም ሰው፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን አሳ​ይህ ዘንድ አንተ ወደ​ዚህ መጥ​ተ​ሃ​ልና በዐ​ይ​ንህ እይ፤ በጆ​ሮ​ህም ስማ፤ የማ​ሳ​ይ​ህ​ንም ሁሉ በል​ብህ ጠብቅ፤ የም​ታ​የ​ው​ንም ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ንገር” አለኝ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ​ቹን ከመ​ከ​ተል ወሰ​ደኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ሂድ፥ ለሕ​ዝቤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ትን​ቢት ተና​ገር አለኝ።


ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከሥርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል፥ እርስዋንም አልጠበቃችሁም። ወደ እኔ ተመለሱ፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተ ግን፦ የምንመለሰው በምንድር ነው? ብላችኋል።


ሙሴና አሮ​ንም ማኅ​በ​ሩን በዐ​ለቷ ፊት ሰብ​ስ​በው፥ “እና​ንተ ዓመ​ፀ​ኞች፥ እን​ግ​ዲህ ስሙ፤ በውኑ ከዚ​ህች ዐለት ውኃን እና​ወ​ጣ​ላ​ችሁ ነበር?” አሏ​ቸው።


“እና​ንተ አን​ገ​ታ​ችሁ የደ​ነ​ደነ፥ ልባ​ች​ሁም የተ​ደ​ፈነ፥ ጆሮ​አ​ች​ሁም የደ​ነ​ቈረ፥ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ዘወ​ትር ትቃ​ወ​ማ​ላ​ችሁ።


“መል​ካ​ሙን የም​ሥ​ራች የሚ​ያ​ወሩ እግ​ሮ​ቻ​ቸው እን​ዴት ያማሩ ናቸው?” ተብሎ እንደ ተጻፈ ካል​ተ​ላኩ እን​ዴት ይሰ​ብ​ካሉ?


ለእ​ና​ንተ ከታ​ወ​ቀ​በት ቀን ጀምሮ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐመ​ፀ​ኞች ነበ​ራ​ችሁ።


በራ​ስህ የማ​ል​ህ​ላ​ቸ​ውን አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን አብ​ር​ሃ​ም​ንና ይስ​ሐ​ቅን፥ ያዕ​ቆ​ብ​ንም አስብ፤ የዚ​ህን ሕዝብ ልበ ደን​ዳ​ና​ነት፥ ክፋ​ቱ​ንም፥ ኀጢ​አ​ቱ​ንም አት​መ​ል​ከት፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos