1 ሳሙኤል 8:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም አለ፥ “በእናንተ ላይ የሚነግሠው የንጉሡ ሥርዐት ይህ ነው፤ ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ሰረገላ ነጂዎችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፤ በሰረገሎችም ፊት ይሮጣሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አለ፤ “በላያችሁ የሚነግሠው ንጉሥ የሚያደርግባችሁ ይህ ነው፤ ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ሠረገለኞችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፤ በሠረገሎቹም ፊት ይሮጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲም አለ፤ “በላያችሁ የሚነግሠው ንጉሥ የሚያደርግባችሁ ይህ ነው፤ ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ሠረገለኞችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፤ በሠረገሎቹም ፊት ይሮጣሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም ሲል ገለጠላቸው፤ “ንጉሣችሁ የሚያደርግባችሁ ነገር ይህ ነው፦ ልጆቻችሁን ወስዶ ሠረገለኞችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፤ አንዳንዶቹም በሠረገሎቹም ፊት የሚሮጡ ያደርጋቸዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም አለ፦ በእናንተ ላይ የሚነግሠው የንጉሡ ወግ ይህ ነው፥ ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ሰረገለኞችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፥ በሰረገሎቹም ፊት ይሮጣሉ፥ |
የአጊትም ልጅ አዶንያስ፥ “ንጉሥ እሆናለሁ” ብሎ ተነሣ፤ ሰረገሎችንና ፈረሰኞችን በፊቱም የሚሮጡ አምሳ ሰዎችን አዘጋጀ።
ሰሎሞንም ለሰረገሎቹ ዐራት ሺህ እንስት ፈረሶች ነበሩት፤ ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሰኞችም ነበሩት፤ በሰረገሎችም ከተሞች ከንጉሡ ጋር በኢየሩሳሌም አኖራቸው። ሰሎሞንም ከወንዙ ጀምሮ እስከ ፍልስጥኤም ምድርና እስከ ግብፅ ድንበር ድረስ በነገሥታቱ ሁሉ ላይ ንጉሥ ነበር።
ከእርሱም ጋር ያደጉት፥ በፊቱ የሚቆሙት ብላቴኖች እንዲህ አሉት፥ “አባትህ ቀንበር አክብዶብናል፥ አንተ ግን ዛሬ አቃልልልን ለሚሉህ ሕዝብ፦ ታናሺቱ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ትወፍራለች።
“አባትህ ቀንበር አክብዶብን ነበር፤ አሁንም አንተ ጽኑውን የአባትህን አገዛዝ፥ በላያችንም የጫነውን የከበደውን ቀንበር አቃልልልን፤ እኛም እንገዛልሃለን።”
ንጉሡም ሮብዓም በፋንታው የናስ ጋሾችን ሠራ፤ በፊቱም ለሚሮጡና የንጉሥን ቤት ደጅ ለሚጠብቁ የዘበኞች አለቆች ሰጣቸው።
የእግዚአብሔርም እጅ በኤልያስ ላይ ነበረች፤ ወገቡንም ታጥቆ ወደ ኢይዝራኤል እስኪገባ ድረስ በአክዓብ ፊት ይሮጥ ነበር።
ሳሙኤልም የንጉሡን ሥርዐት ነገራቸው፤ በመጽሐፍም ጻፈው፤ በእግዚአብሔርም ፊት አኖረው። ሳሙኤልም ሕዝቡን ሁሉ ወደ እየቤታቸው አሰናበታቸው። ሕዝቡም ሁሉ ወደ እየቤታቸው ሄዱ።
በሳኦልም ዘመን ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጽኑ ውጊያ ነበረ፤ ሳኦልም ጽኑ ወይም ኀያል ሰው ባየ ጊዜ ወደ እርሱ ይሰበስብ ነበር።
ሳኦልም በአጠገቡ የቆሙትን ብላቴኖች፥ “ብንያማውያን ሆይ! እንግዲህ ስሙ በእውነት የእሴይ ልጅ እርሻና የወይን ቦታ ለሁላችሁ ይሰጣችኋልን? ሁላችሁንስ መቶ አለቆችና ሻለቆች ያደርጋችኋልን?
አሁንም ቃላቸውን ስማ፤ ነገር ግን ጽኑ ምስክር መስክርባቸው፤ በእነርሱም ላይ የሚነግሠውን የንጉሡን ሥርዐት ንገራቸው።”