Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ሳሙኤል 8:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እንዲህም አለ፤ “በላያችሁ የሚነግሠው ንጉሥ የሚያደርግባችሁ ይህ ነው፤ ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ሠረገለኞችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፤ በሠረገሎቹም ፊት ይሮጣሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እንዲም አለ፤ “በላያችሁ የሚነግሠው ንጉሥ የሚያደርግባችሁ ይህ ነው፤ ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ሠረገለኞችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፤ በሠረገሎቹም ፊት ይሮጣሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እንዲህም ሲል ገለጠላቸው፤ “ንጉሣችሁ የሚያደርግባችሁ ነገር ይህ ነው፦ ልጆቻችሁን ወስዶ ሠረገለኞችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፤ አንዳንዶቹም በሠረገሎቹም ፊት የሚሮጡ ያደርጋቸዋል፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እን​ዲ​ህም አለ፥ “በእ​ና​ንተ ላይ የሚ​ነ​ግ​ሠው የን​ጉሡ ሥር​ዐት ይህ ነው፤ ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን ወስዶ ሰረ​ገላ ነጂ​ዎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም ፊት ይሮ​ጣሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እንዲህም አለ፦ በእናንተ ላይ የሚነግሠው የንጉሡ ወግ ይህ ነው፥ ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ሰረገለኞችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፥ በሰረገሎቹም ፊት ይሮጣሉ፥

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 8:11
14 Referencias Cruzadas  

በሳኦል ዘመን ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋራ ከባድ ጦርነት ነበረ፤ ስለዚህ ሳኦል ብርቱ ወይም ጀግና ሰው ባየ ቍጥር ወደ ራሱ ወስዶ እንዲያገለግለው ያደርግ ነበር።


ሳሙኤልም ለንጉሥ የሚገባውን ወግና ሥርዐት ለሕዝቡ ገልጾ ካስረዳ በኋላ በመጽሐፍ ጽፎ በእግዚአብሔር ፊት አኖረው። ከዚህ በኋላ ሳሙኤል እያንዳንዱን ሰው ወደየቤቱ አሰናበተ።


ከዚህ በኋላ አቤሴሎም ሠረገላና ፈረሶች እንዲሁም ፊት ፊቱ የሚሮጡ ዐምሳ ሰዎች ለራሱ አዘጋጀ።


ሰሎሞን ሠረገሎችንና ፈረሶችን ሰበሰበ፤ እርሱም አንድ ሺሕ አራት መቶ ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት ሺሕ ፈረሶች ነበሩት፤ እነርሱንም በሠረገላ ከተሞችና ንጉሡ ባለበት በኢየሩሳሌም ከተማ አኖራቸው።


የእግዚአብሔርም ኀይል በኤልያስ ላይ ወረደ፤ ኤልያስም ልብሱን ከፍ አድርጎ በቀበቶው ካጠበቀ በኋላ፣ እስከ ኢይዝራኤል ድረስ አክዓብን ቀድሞት ሮጠ።


ዐብሮ አደጎቹም ወጣቶች እንዲህ አሉት፤ “ ‘አባትህ በላያችን ከባድ ቀንበር ጫነብን፣ አንተ ግን ቀንበራችንን አቅልልልን’ ለሚሉህ ለእነዚህ ሰዎች፣ ‘ትንሿ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ይልቅ ትወፍራለች፤


“አባትህ ቀንበራችንን አከበደብን፤ አንተ ግን አሁን አስጨናቂውን ሥራና በላያችን የጫነብንን ከባድ ቀንበር አቅልልልን፤ እኛም እንገዛልሃለን” አሉት።


በዚህ ጊዜ ከአጊት የተወለደው አዶንያስ፣ “እነግሣለሁ” ብሎ ተነሣ፤ ስለዚህ ሠረገሎችንና ፈረሶችን እንዲሁም ከፊት ከፊቱ የሚሄዱ ዐምሳ ሰዎችን አዘጋጀ።


አሁን የሚሉህን ስማቸው፤ በላያቸው የሚነግሠው ንጉሥ ምን እንደሚፈጽምባቸውም አሳውቃቸው፤ በሚገባም አስጠንቅቃቸው።”


ስለዚህ ንጉሥ ሮብዓም እነዚህን ለመተካት ሲል፣ የናስ ጋሻዎች ሠርቶ የቤተ መንግሥቱን ቅጥር በር ለሚጠብቁ የዘብ አለቆች በኀላፊነት ሰጠ።


ሳኦልም እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ የብንያም ሰዎች ስሙ! በውኑ የእሴይ ልጅ ዕርሻና የወይን ቦታ ለሁላችሁ ይሰጣችኋልን? ሁላችሁንስ ሻለቆችና የመቶ አለቆች ያደርጋችኋልን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios