1 ሳሙኤል 31:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሸለቆውም ማዶና በዮርዳኖስ ማዶ የነበሩ እስራኤላውያን የእስራኤል ሰዎች እንደ ሸሹ፥ ሳኦልና ልጆቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተሞቹን ለቅቀው ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሸለቆው ማዶና ከዮርዳኖስ ባሻገር ያሉ እስራኤላውያን፣ የእስራኤል ሰራዊት መሸሹን፣ ሳኦልና ልጆቹም መሞታቸውን ሲያዩ፣ ከተሞቻቸውን ለቅቀው ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሸለቆው ማዶና ከዮርዳኖስ ባሻገር ያሉ እስራኤላውያን የእስራኤል ሠራዊት መሸሹን፥ ሳኦልና ልጆቹም መሞታቸውን ባዩ ጊዜ ከተሞቻቸውን ለቀው ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅና በኢይዝራኤል ሸለቆ ማዶ የነበሩ እስራኤላውያንም የእስራኤል ሠራዊት መሸሹን፥ ሳኦልና ልጆቹም መገደላቸውን ሰምተው ከተሞቻቸውን እየጣሉ ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ከተሞቹን ያዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሸለቆውም ማዶና በዮርዳኖስ ማዶ የነበሩ እስራኤላውያን የእስራኤል ሰዎች እንደ ሸሹ፥ ሳኦልና ልጆቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተማቹን ለቅቀው ሸሹ፥ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው። |
በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ ተለይተው በቀሩት ላይ በልባቸው ድንጋጤን እሰድድባቸዋለሁ፤ በነፋስም የምትንቀሳቀስ የቅጠል ድምፅ ታሸብራቸዋለች፤ ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሸሻሉ ፤
የምድርህን ፍሬ፥ ድካምህንም ሁሉ የማታውቀው ሕዝብ ይበላዋል፤ አንተም ሁልጊዜ የተጨነቅህ፥ የተገፋህም ትሆናለህ።
የምድያምም እጅ በእስራኤል ላይ ጠነከረች፤ ከምድያምም ፊት የተነሣ የእስራኤል ልጆች በተራሮችና በገደሎች ላይ ጕድጓድና ዋሻ፥ ምሽግም አበጁ።
የእስራኤልም ሰዎች ወደ እነርሱ መሄድ እንደሚያስጨንቃቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ በዋሻና በግንብ፥ በገደልና በቋጥኝ፥ በጕድጓድም ውስጥ ተሸሸጉ።
ዮርዳኖስንም ተሻግረው ወደ ጋድና ወደ ገለዓድ ምድር የሄዱ አሉ፤ ሳኦል ግን ገና በጌልጌላ ነበረ፤ ሕዝቡም ሁሉ ፈርተው እርሱን መከተልን ትተው ተበተኑ።
በማግሥቱም ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ለመግፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦልና ሦስቱ ልጆቹ በጌላቡሄ ተራራ ላይ ወድቀው አገኙአቸው።