አቤቱ ይህ ለአንተ አግባብ አይደለም፤ ይህን ነገር አታድርግ፤ ጻድቃንን ከኃጥኣን ጋር አታጥፋ፤ ምድርን ሁሉ የምትገዛ ይህን ፍርድ ታደርግ ዘንድ ለአንተ አግባብ አይደለም።”
1 ሳሙኤል 3:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም ነገሩን ሁሉ ነገረው፤ አንዳችም አልሸሸገውም። ዔሊም፥ “እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ደስ ያሰኘውን ያድርግ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሳሙኤል ምንም ነገር ሳይደብቅ ሁሉንም ነገረው። ዔሊም፣ “እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ መልካም መስሎ የታየውን ያድርግ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ሳሙኤል ምንም ነገር ሳይደብቅ ሁሉንም ነገረው። ዔሊም፥ “እርሱ ጌታ ነው፤ ደስ ያሰኘውን ያድርግ” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ሳሙኤል ሁሉንም ነገር ለዔሊ አስረዳው፤ ሰውሮ ያስቀረው ምንም ነገር አልነበረም፤ ዔሊም “እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህም መልካም መስሎ የታየውን ነገር ያድርግ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም ነገሩን ሁሉ ነገረው፥ አንዳችም አልሸሸገውም። ዔሊም፦ እርሱ እግዚአብሔር ነው፥ ደስ ያሰኘውን ያድርግ አለ። |
አቤቱ ይህ ለአንተ አግባብ አይደለም፤ ይህን ነገር አታድርግ፤ ጻድቃንን ከኃጥኣን ጋር አታጥፋ፤ ምድርን ሁሉ የምትገዛ ይህን ፍርድ ታደርግ ዘንድ ለአንተ አግባብ አይደለም።”
በርታ፤ ስለ ሕዝባችንና ስለ አምላካችንም ከተሞች እንጽና፤ እግዚአብሔርም በዐይኑ ፊት ደስ ያሰኘውን መልካሙን ያድርግ።”
አይዞህ፥ በርታ፤ ስለ ሕዝባችንና ስለ አምላካችንም ከተሞች እንበርታ፤ እግዚአብሔርም በፊቱ ደስ ያሰኘውን ያድርግ” አለ።
እንዲህም አለ፥ “ከእናቴ ማኅፀን ራቁቴን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደ ምድር እመለሳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፥ እግዚአብሔርም ነሣ፤ እግዚአብሔርም እንደ ፈቀደ ሆነ የእግዚአብብሔር ስም የተባረከ ይሁን።”
እርሱ ግን፦ ወደ እርስዋ ተመለከተና እንዲህ አላት፥ “አንቺ ከሰነፎች ሴቶች እንደ አንዲቱ ተናገርሽ፤ ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ተቀበልን፥ ክፉውን ነገርስ አንታገሥምን?” በዚህ በደረሰበት ሁሉ ኢዮብ በእግዚአብሔር ፊት በከንፈሩ አልበደለም።
ሕዝቅያስም ኢሳይያስን፥ “እርሱ የተናገረው የእግዚአብሔር ቃል መልካም ነው፤ ነገር ግን፦ በዘመኔ ሰላምና ጽድቅ ይሁን” አለው።
ንጉሡም ሴዴቅያስ ልኮ በእግዚአብሔር ቤት ወደ ነበረው ወደ ሦስተኛው መግቢያ ወደ እርሱ ነቢዩን ኤርምያስን አስመጣው፤ ንጉሡም ኤርምያስን፥ “አንዲት ነገር እጠይቅሃለሁ፤ ምንም አትሸሽገኝ” አለው።
ነቢዩ ኤርምያስም አላቸው፥ “ሰምታችኋል፤ እነሆ እንደ ቃላችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ እግዚአብሔርም የሚመልስልኝን ሁሉ እነግራችኋለሁ፤ ከእናንተም አንድም ቃል አልሸሽግም።”
ሙሴም አሮንን፥ “እግዚአብሔር፦ ወደ እኔ በሚቀርቡ እመሰገናለሁ፤ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ ብሎ የተናገረው ይህ ነው” አለው፤ አሮንም ደነገጠ።
የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔርን፥ “እኛ ኀጢአትን ሠርተናል፤ አንተ በፊትህ ደስ የሚያሰኝህን አድርግብን፤ ዛሬ ግን እባክህ አድነን” አሉት።