Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 19:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 አይ​ዞህ፥ በርታ፤ ስለ ሕዝ​ባ​ች​ንና ስለ አም​ላ​ካ​ች​ንም ከተ​ሞች እን​በ​ርታ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፊቱ ደስ ያሰ​ኘ​ውን ያድ​ርግ” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እንግዲህ በርቱ፤ ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች በጀግንነት እንዋጋ፤ እግዚአብሔርም በፊቱ ደስ ያሠኘውን ያድርግ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 አይዞህ፥ ስለ ሕዝባችንና ስለ አምላካችንም ከተሞች እንበርታ፤ ጌታም ደስ ያሰኘውን ያድርግ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እንግዲህ አይዞህ በርታ! ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተማዎች ስንል በርትተን እንዋጋ፤ ለዚህም የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 አይዞህ! ስለ ሕዝባችንና ስለ አምላካችንም ከተሞች እንበርታ፤ እግዚአብሔርም ደስ ያሰኘውን ያድርግ፤” አለ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 19:13
18 Referencias Cruzadas  

በርታ፤ ስለ ሕዝ​ባ​ች​ንና ስለ አም​ላ​ካ​ች​ንም ከተ​ሞች እን​ጽና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዐ​ይኑ ፊት ደስ ያሰ​ኘ​ውን መል​ካ​ሙን ያድ​ርግ።”


ነገር ግን አል​ወ​ድ​ድ​ህም ቢለኝ፥ እነ​ሆኝ በፊቱ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን ያድ​ር​ግ​ብኝ” አለው።


ኢዮ​አ​ብም፥ “ሶር​ያ​ው​ያን ቢበ​ረ​ቱ​ብኝ ርዳኝ፤ የአ​ሞ​ንም ልጆች ቢበ​ረ​ቱ​ብህ እረ​ዳ​ሃ​ለሁ።


ኢዮ​አ​ብና ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ረው ሕዝብ ከሶ​ር​ያ​ው​ያን ጋር ተዋጉ፤ እነ​ር​ሱም ከፊ​ታ​ቸው ሸሹ።


ይህም ነገር ለአ​ንተ ይገ​ባ​ልና፥ እኛም ከአ​ንተ ጋር ነንና ተነሣ፤ በርታ፤ አድ​ር​ገ​ውም።”


አይ​ችም ተነ​ሣሁ፤ ታላ​ላ​ቆ​ቹ​ንና ሹሞ​ቹ​ንም፥ የቀ​ሩ​ት​ንም ሕዝብ፥ “አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው፤ ታላ​ቁ​ንና የተ​ፈ​ራ​ውን አም​ላ​ካ​ች​ንን አስቡ፤ ስለ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁም፥ ስለ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም፥ ስለ ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁም፥ ስለ ቤቶ​ቻ​ች​ሁም ተዋጉ” አል​ኋ​ቸው።


በዚ​ህም በደ​ረ​ሰ​በት ሁሉ ኢዮብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አል​በ​ደ​ለም፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስን​ፍ​ናን አል​ሰ​ጠም።


ትጉ፤ በሃ​ይ​ማ​ኖ​ትም ቁሙ፤ ታገሡ ጽኑ፤


አገ​ል​ጋዬ ሙሴ እንደ አዘ​ዘህ ሕግን ሁሉ ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ ጽና፤ እጅ​ግም በርታ፤ ሁሉን እን​ዴት እን​ደ​ም​ት​ሠራ ታውቅ ዘንድ ከእ​ርሱ ወደ ቀኝ ወደ ግራም አት​በል።


ኢያ​ሱም፥ “በም​ት​ወ​ጉ​አ​ቸው በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ሁሉ ላይ እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ር​ጋ​ልና አት​ፍሩ፤ አት​ደ​ን​ግጡ፤ ጽኑ፤ አይ​ዞ​አ​ችሁ” አላ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “እኛ ኀጢ​አ​ትን ሠር​ተ​ናል፤ አንተ በፊ​ትህ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን አድ​ር​ግ​ብን፤ ዛሬ ግን እባ​ክህ አድ​ነን” አሉት።


ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን፥ “ስለ እርሱ የማ​ንም ልብ አይ​ው​ደቅ፤ እኔ ባሪ​ያህ ሄጄ ያን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ እወ​ጋ​ዋ​ለሁ” አለው።


ሳሙ​ኤ​ልም ነገ​ሩን ሁሉ ነገ​ረው፤ አን​ዳ​ችም አል​ሸ​ሸ​ገ​ውም። ዔሊም፥ “እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ደስ ያሰ​ኘ​ውን ያድ​ርግ” አለ።


እና​ንተ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሆይ! በርቱ፤ ጐብዙ፤ እና​ንተ ባሪ​ያ​ዎች እን​ዳ​ደ​ረ​ጋ​ች​ኋ​ቸው ዕብ​ራ​ው​ያን ባሪ​ያ​ዎች እን​ዳ​ያ​ደ​ር​ጓ​ችሁ በርቱ፤ ተዋጉ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos