Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 19:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 አይዞህ፥ ስለ ሕዝባችንና ስለ አምላካችንም ከተሞች እንበርታ፤ ጌታም ደስ ያሰኘውን ያድርግ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እንግዲህ በርቱ፤ ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች በጀግንነት እንዋጋ፤ እግዚአብሔርም በፊቱ ደስ ያሠኘውን ያድርግ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እንግዲህ አይዞህ በርታ! ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተማዎች ስንል በርትተን እንዋጋ፤ ለዚህም የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 አይ​ዞህ፥ በርታ፤ ስለ ሕዝ​ባ​ች​ንና ስለ አም​ላ​ካ​ች​ንም ከተ​ሞች እን​በ​ርታ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፊቱ ደስ ያሰ​ኘ​ውን ያድ​ርግ” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 አይዞህ! ስለ ሕዝባችንና ስለ አምላካችንም ከተሞች እንበርታ፤ እግዚአብሔርም ደስ ያሰኘውን ያድርግ፤” አለ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 19:13
18 Referencias Cruzadas  

በጌታ ተስፋ አድርግ፥ በርታ፥ ልብህም ይጽና፥ በጌታ ተስፋ አድርግ።


የቀንደ መለከቱን ድምፅ በምትሰሙበት ስፍራ በዚያ ወደ እኛ ተሰብሰቡ፤ አምላካችን ስለ እኛ ይዋጋል።”


እንግዲህ በርታ፤ ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች በጀግንነት እንዋጋ፤ ጌታም በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያድርግ።”


ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ “ጌታ በምትወጉአቸው በጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ እንዲሁ ያደርጋልና አትፍሩ፥ አትደንግጡ፤ ጽኑ፥ አይዞአችሁ።”


ንቁ፤ በእምነት ጽኑ፤ በርቱ፤ ጠንክሩ፤


ፍልስጥኤማውያን ሆይ፤ በርቱ! ወንድነታችሁም ይታይ፤ ያለዚያ ባርያ እንዳደረጋችኋቸው ሁሉ፥ ዕብራውያን እናንተን መልሰው ባርያ ያደርጓችኋል። ስለዚህ በወንድነት ጠንክራችሁ ተዋጉ!”


ተነሥ ይህም ነገር የአንተ ሥራ ነውና፥ እኛም ከአንተ ጋር እንሆናለን፤ በርታ፥ አድርገውም።”


ዳዊትም ሳኦልን፥ “ከዚህ ፍልስጥኤማዊ የተነሣ የማንም ሰው ልብ አይሸበር፤ እኔ አገልጋይህ ሄጄ እዋጋዋለሁ” አለው።


እስራኤላውያንም ጌታን፥ “ኃጢአት ሠርተናል፤ መልካም መስሎ የታየህን አድርግብን፤ እባክህን የዛሬን ብቻ አድነን” አሉት።


ነገር ግን ጽና፥ እጅግም በርታ፤ ባርያዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ ሁሉ ጠብቅ፥ አድርገውም፤ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ከእርሱ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል።


በዚህ ሁሉ ኢዮብ አልበደለም፥ እግዚአብሔርንም አላማረረም።


ነገር ግን እርሱ፥ ‘ባንተ አልተደሰትሁም’ የሚል ከሆነ፥ እነሆኝ፥ መልካም መስሎ የታየውን ነገር ያድርግብኝ።”


ስለዚህ ሳሙኤል ምንም ነገር ሳይደብቅ ሁሉንም ነገረው። ዔሊም፥ “እርሱ ጌታ ነው፤ ደስ ያሰኘውን ያድርግ” አለ።


እርሱም እንዲህ አለ፦ “ሶርያውያን ቢበረቱብኝ እርዳኝ፤ የአሞንም ልጆች ቢበረቱብህ እረዳሃለሁ።


ኢዮአብና ከእርሱም ጋር የነበረው ሕዝብ ለውግያ ወደ ሶርያውያን ፊት ቀረቡ፥ እነርሱም ከፊቱ ሸሹ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios