1 ሳሙኤል 29:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም አንኩስን፥ “ምን አድርጌአለሁ? ሄጄስ ከጌታዬ ከንጉሡ ጠላቶች ጋር እንዳልዋጋ፥ በፊትህ ከተቀመጥሁ ጀምሬ እስከ ዛሬ ድረስ በእኔ በአገልጋይህ ምን በደል አግኝተህብኛል?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም አንኩስን፣ “ለመሆኑ ምን አደረግሁ? እዚህ ከመጣሁበት ዕለት ጀምሮ እስካሁን ድረስ፣ በአገልጋይህ ላይ ምን አገኘህበት? ታዲያ፣ ከንጉሡ ከጌታዬ ጠላቶች ጋራ የማልዋጋው ስለ ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም ለአኪሽ፥ “ለመሆኑ ምን አደረግሁ? እዚህ ከመጣሁበት ዕለት ጀምሮ እስካሁን ድረስ፥ በአገልጋይህ ላይ ምን አገኘህበት? ታዲያ፥ ከንጉሡ ከጌታዬ ጠላቶች ጋር የማልዋጋው ስለ ምንድነው?” ብሎ ጠየቀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም “ጌታዬ ምን በደል ሠራሁ? አንተን ማገልገል ከጀመርኩበት ጊዜ አንሥቶ በደል ካልተገኘብኝ ጌታዬና ንጉሤ የሆንከውን አንተን ተከትዬ በመዝመት ጠላቶችህን መውጋት የማልችለው ስለምንድን ነው?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም አንኩስን፦ ምን አድርጌአለሁ? ሄጄስ ከጌታዬ ከንጉሡ ጠላቶች ጋር እንዳልዋጋ፥ በፊትህ ከተቀመጥሁ ጀምሬ እስከ ዛሬ ድረስ በእኔ በባሪያህ ምን አግኝተህብኛል? አለው። |
እነሆኝ፥ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንንስ አህያ ወሰድሁ? ማንንስ ሸነገልሁ? በማንስ ላይ ግፍ አደረግሁ? ነጠላ ጫማ እንኳን ቢሆን ከማን እጅ መማለጃ ተቀበልሁ? መስክሩብኝ፤ እኔ እመልስላችኋለሁ።”
እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ከባሪያህ ጋር አድርገሃልና ለባሪያህ ቸርነትን አድርግ፤ በደል ግን ቢገኝብኝ አንተ ግደለኝ፤ ለምን ወደ አባትህ ታደርሰኛለህ?”
አንኩስም ዳዊትን፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” አለው፤ ዳዊትም፥ “በይሁዳ ደቡብ፥ በያሴሜጋ ደቡብ፥ በቄኔዛውያን ደቡብ ላይ ዘመትን” አለው።
ዳዊትም አንኩስን፥ “አሁን አገልጋይህ የሚያደርገውን ንገረው” አለው። አንኩስም ዳዊትን፥ “እንግዲህ በዘመኑ ሁሉ ራሴን ጠባቂ አደርግሃለሁ” አለው።