1 ሳሙኤል 21:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም አቤሜሌክን፥ “የንጉሥ ጉዳይ ስላስቸኰለኝ ሰይፌንና መሣሪያዬን አላመጣሁምና በአንተ ዘንድ ጦር ወይም ሰይፍ እንዳለ እይልኝ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት አቢሜሌክን፣ “የንጉሡ ጕዳይ ስላስቸኰለኝ፣ ሰይፌንም ሆነ ሌላ የጦር መሣሪያ አላመጣሁም፤ እዚህ ካንተ ዘንድ ጦር ወይም ሰይፍ አይገኝምን?” ሲል ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት አቢሜሌክን፥ “የንጉሡ ጉዳይ ስላስቸኮለኝ፥ ሰይፌንም ሆነ ሌላ የጦር መሣሪያ አላመጣሁም፤ እዚህ ካንተ ዘንድ ጦር ወይም ሰይፍ አይገኝምን?” ሲል ጠየቀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም አቤሜሌክን “የምትሰጠኝ ጦር ወይም ሰይፍ በአንተ ዘንድ ይገኛልን? የንጉሡ ትእዛዝ አስቸኳይ ስለ ሆነ ጦሬንም ሆነ ሌላውንም መሣሪያዬን ለመያዝ ጊዜ አላገኘሁም ነበር” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም አቢሜሌክን፦ የንጉሥ ጉዳይ ስላስቸኮለኝ ሰይፌንና መሣሪያዬን አላመጣሁምና በአንተ ዘንድ ጦር ወይም ሰይፍ አለ ወይ? አለው። |
በዚያም ቀን ከሳኦል አገልጋዮች አንድ ሰው በኔሴራ አቅራቢያ በዚያ በእግዚአብሔር ፊት ነበር፤ ስሙም ሶርያዊው ዶይቅ ነበረ፤ የሳኦልም በቅሎዎች ጠባቂ ነበረ።
ካህኑም፥ “በኤላ ሸለቆ የገደልኸው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ እነሆ፥ በመጐናጸፊያ ተጠቅልላ አለች፤ የምትወስዳት ከሆነ ውሰዳት፤ ከእርስዋ በቀር ሌላ ከዚህ የለምና” አለው። ዳዊትም፥ “ከእርስዋ በቀር ሌላ ከሌለ እርስዋን ስጠኝ” አለው። እርሱም ሰጠው።
ዳዊት አብያታርን፦ ሶርያዊው ዶይቅ በዚያ መኖሩን ባየሁ ጊዜ፥ “ለሳኦል በርግጥ ይነግራል ብዬ በዚያ ቀን አውቄዋለሁ፤ ለአባትህ ቤት ነፍስ ሁሉ ጥፋት በደለኛው እኔ ነኝ።
የሳኦልም በቅሎዎች ጠባቂ ሶርያዊው ዶይቅ መልሶ፥ “የእሴይ ልጅ ወደ ኖብ ወደ አኪጦብ ልጅ ወደ ካህኑ አቤሜሌክ ሲመጣ አይቼዋለሁ።