Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሉቃስ 10:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከረ​ጢ​ትም፥ ስል​ቻም፥ ጫማም፥ ምንም ምን አት​ያዙ፤ በመ​ን​ገ​ድም ማን​ንም ሰላም አት​በሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ኰረጆ ወይም ከረጢት ወይም ጫማ አትያዙ፤ በመንገድ ላይም ለማንም ሰላምታ አትስጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ቦርሳም ከረጢትም ጫማም አትያዙ፤ በመንገድ ላይ ለማንም ሰላምታን አትስጡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ለመንገዳችሁ ምንም አትያዙ፤ የገንዘብ ቦርሳም ቢሆን፥ ከረጢትም ቢሆን፥ ጫማም ቢሆን አትያዙ፤ ከሰው ጋር ሰላምታ በመለዋወጥ በመንገድ ላይ ቆማችሁ ጊዜ አታጥፉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ኮረጆም ከረጢትም ጫማም አትያዙ፤ በመንገድም ለማንም እጅ አትንሡ።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 10:4
13 Referencias Cruzadas  

ይበ​ላም ዘንድ እን​ጀ​ራን አቀ​ረ​ቡ​ለት፤ እርሱ ግን “ነገ​ሬን እስ​ክ​ና​ገር ደረስ አል​በ​ላም” አለ። እነ​ር​ሱም “ተና​ገር” አሉት።


እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገ​ዴን አቅ​ን​ቶ​ልኝ ሳለ አታ​ዘ​ግ​ዩኝ፤ ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰ​ና​ብ​ቱኝ” አላ​ቸው።


አህ​ያ​ው​ንም አስ​ጭና ሎሌ​ዋን፥ “ንዳ፥ ሂድ፤ እኔ ሳላ​ዝ​ዝህ አታ​ዘ​ግ​የኝ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ ቄር​ሜ​ሎስ ተራራ እን​ሂድ” አለ​ችው።


ኤል​ሳ​ዕም ግያ​ዝን፥ “ወገ​ብ​ህን ታጠቅ፤ በት​ሬ​ንም በእ​ጅህ ይዘህ ሂድ፤ ሰውም ብታ​ገኝ ሰላም አት​በል፤ እር​ሱም ሰላም ቢልህ አት​መ​ል​ስ​ለት፤ በት​ሬ​ንም በሕ​ፃኑ ፊት ላይ አኑር” አለው።


ዐይኖችህም አቅንተው ይዩ፥ ሽፋሽፍቶችህም ወደ እውነት ያመልክቱ።


ዐሥራ ሁለቱንም ወደ እርሱ ጠራ፤ ሁለት ሁለቱንም ይልካቸው ጀመር፤ በርኵሳን መናፍስትም ላይ ሥልጣን ሰጣቸው፤


ደግ​ሞም፥ “ያለ ስልቻ፥ ያለ ከረ​ጢ​ትና ያለ ጫማ በላ​ክ​ኋ​ችሁ ጊዜ በውኑ የተ​ቸ​ገ​ራ​ች​ሁት ነገር ነበ​ርን?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “የለም” አሉት።


ዳዊ​ትም አቤ​ሜ​ሌ​ክን፥ “የን​ጉሥ ጉዳይ ስላ​ስ​ቸ​ኰ​ለኝ ሰይ​ፌ​ንና መሣ​ሪ​ያ​ዬን አላ​መ​ጣ​ሁ​ምና በአ​ንተ ዘንድ ጦር ወይም ሰይፍ እን​ዳለ እይ​ልኝ” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos