1 ሳሙኤል 21:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ይህን ቃል በልቡ አኖረ፤ የጌትንም ንጉሥ አንኩስን እጅግ ፈራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት ነገሩን በልቡ አኖረ፤ የጋትን ንጉሥ አንኩስንም እጅግ ፈራው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት ነገሩን በልቡ አኖረ፤ የጋትን ንጉሥ አኪሽንም እጅግ ፈራው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእነርሱም አነጋገር የዳዊት ልብ በብርቱ ተነካ፤ ንጉሥ አኪሽንም በብርቱ ፈራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ይህን ቃል በልቡ አኖረ፥ የጌትንም ንጉሥ አንኩስን እጅግ ፈራ። |
ከእነርሱም ጋር ሂዶ ወደ ናዝሬት ወረደ፤ ይታዘዝላቸውም ነበር፤ እናቱ ግን ይህን ሁሉ ነገር ትጠብቀው፥ በልብዋም ታኖረው ነበር።
በፊቱም መልኩን ለወጠ፤ በዚያችም ቀን አመለጠ። በከተማውም በር ከበሮ ይዞ በእጁ መታ፤ በበሩም መድረክ ላይ ተንፈራፈረ፤ ልጋጉም በጢሙ ላይ ይወርድ ነበር።