1 ሳሙኤል 21:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ወደ ካህኑ ወደ አቤሜሌክ ወደ ኖብ መጣ፤ አቤሜሌክም እርሱን በተገናኘው ጊዜ ደነገጠ፥ “ስለምን አንተ ብቻህን ነህ? ከአንተስ ጋር ስለምን ማንም የለም?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም ካህኑ አቢሜሌክ ወዳለበት ወደ ኖብ ሄደ። አቢሜሌክም እየተንቀጠቀጠ ዳዊትን ሊገናኘው መጣና፣ “ምነው ብቻህን? ሰውስ ለምን ዐብሮህ የለም?” ሲል ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም ካህኑ አቢሜሌክ ወዳለበት ወደ ኖብ ሄደ። አቢሜሌክም እየተንቀጠቀጠ ዳዊትን ሊገናኘው መጣና፥ “ምነው ብቻህን? ሰውስ ለምን አብሮህ የለም?” ሲል ጠየቀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት በኖብ ወደሚገኘው ወደ ካህኑ አቤሜሌክ ዘንድ ሄደ፤ አቤሜሌክም በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ ሊቀበለው ወጥቶ “ማንም ሰው ሳይከተልህ ብቻህን ስለምን ወደዚህ መጣህ?” ሲል ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ወደ ካህኑ ወደ አቢሜሌክ ወደ ኖብ መጣ፥ አቢሜሌክም እየተንቀጠቀጠ ዳዊትን ሊገናኘው መጣና፦ ስለ ምን አንተ ብቻህን ነህ? ከአንተስ ጋር ስለምን ማንም የለም? አለው። |
አብያተር ሊቀ ካህናት በነበረ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ገባ፥ ከካህናት በቀር መብላት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕትን እንጀራ እንደ በላ፥ ከእርሱም ጋር ለነበሩት እንደ ሰጣቸው ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው።
የዔሊ ልጅ፥ የፊንሐስ ልጅ፥ የዮካብድ ወንድም፥ የአኪጦብ ልጅ በሴሎ ለእግዚአብሔር ካህን የሆነ፥ ኤፉድም የለበሰ አኪያ አብሮ ነበር፤ ሕዝቡም ዮናታን እንደ ሄደ አላወቁም ነበር።
ሳሙኤልም እግዚአብሔር የተናገረውን አደረገ፤ ወደ ቤተ ልሔምም መጣ። የከተማውም ሽማግሌዎች በተገናኙት ጊዜ ደነገጡ፥ “ነቢይ! የመጣኸው ለሰላም ነውን?” አሉት።