1 ሳሙኤል 18:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ፥ ከሳኦልም ስለ ተለየ ሳኦል ከዳዊት ፊት የተነሣ ፈራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ከርሱ ተለይቶ ከዳዊት ጋራ ስለ ሆነ፣ ሳኦል ዳዊትን ፈራው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ከእርሱ ተለይቶ ከዳዊት ጋር ስለሆነ ሳኦል ዳዊትን ፈራው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እርሱን ትቶ ከዳዊት ጋር ስለ ነበረ ሳኦል ዳዊትን ፈራው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ ከሳኦልም ስለ ተለየ ሳኦል ዳዊትን ፈራው። |
እግዚአብሔርም ከኢዮሳፍጥ ጋር ነበረ፤ በፊተኛዪቱም በአባቱ በዳዊት መንገድ ሄዶአልና፥ ጣዖትንም አልፈለገምና፤
ሄሮድስ ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ ሰው እንደ ሆነ አውቆ ይፈራውና ይጠባበቀው ነበር፤ እርሱንም ሰምቶ በብዙ ነገር ያመነታ ነበር፤ በደስታም ይሰማው ነበር።
በጌርጌሴኖንም ዙሪያ ያሉ ሰዎች ከእነርሱ ዘንድ እንዲሄድላቸው ማለዱት፤ ጽኑ ፍርሀት ይዞአቸዋልና፤ ጌታችን ኢየሱስም በታንኳ ሆኖ ተመለሰ።
እርሱም ስለ ጽድቅና ስለ ንጽሕና፥ ስለሚመጣውም ኵነኔ በነገራቸው ጊዜ በዚህ የተነሣ ፊልክስ ፈራና ጳውሎስን፥ “አሁንስ ሂድ፤ በተመቸኝም ጊዜ ልኬ አስጠራሃለሁ” አለው።
እግዚአብሔርም ከይሁዳ ጋር ነበረ፤ ይሁዳም ተራራማውን ሀገር ወረሰ፤ በሸለቆው የሚኖሩትን ግን የብረት ሰረገሎች ነበሩአቸውና ሊወርሳቸው አልቻለም።
ደሊላም፥ “ሶምሶን ሆይ! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። ከእንቅልፉም ነቅቶ፥ “እወጣለሁ፤ እንደ ወትሮውም ጊዜ አደርጋለሁ፤ አጠፋቸዋለሁም” አለ። ነገር ግን እግዚአብሔር ከእርሱ እንደ ተለየው አላወቀም።
ከብላቴኖቹም አንዱ መልሶ፥ “እነሆ፥ መልካም አድርጎ በገና ሲመታ የቤተ ልሔሙን የእሴይን ልጅ አይቻለሁ፤ ሰውየውም ጠቢብ፥ ተዋጊም ነው፤ በነገርም ብልህ፥ መልኩም ያማረ ነው፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነው” አለ።
ሳሙኤልም እግዚአብሔር የተናገረውን አደረገ፤ ወደ ቤተ ልሔምም መጣ። የከተማውም ሽማግሌዎች በተገናኙት ጊዜ ደነገጡ፥ “ነቢይ! የመጣኸው ለሰላም ነውን?” አሉት።
አባቴም በአንተ ላይ ክፋት ማድረግ ቢወድድ፥ እኔም ባላስታውቅህ፥ በሰላምም ትሄድ ዘንድ ባላሰናብትህ፥ እግዚአብሔር በዮናታን ይህን ያድርግ፤ ይህንም ይጨምር፤ እግዚአብሔርም ከአባቴ ጋር እንደ ነበረ ከአንተ ጋር ይሁን።
ሳኦልም፥ “አንተ ከእሴይ ልጅ ጋር ለምን ዶለትህብኝ? እንጀራና ሰይፍ ሰጠኸው፤ ዛሬም እንደ ተደረገው ጠላት ሆኖ ይነሣብኝ ዘንድ እግዚአብሔርን ስለ እርሱ ጠየቅህለት” አለው።
ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “ለምን አወክኸኝ? ለምንስ አስነሣኸኝ?” አለው። ሳኦልም መልሶ፥ “ፍልስጥኤማውያን ይወጉኛልና እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ እግዚአብሔርም ከእኔ ርቆአል፤ በነቢያት ወይም በሕልም አላሚዎች አልመለሰልኝም፤ ስለዚህም የማደርገውን ታስታውቀኝ ዘንድ ጠራሁህ” አለው።