1 ሳሙኤል 14:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሳኦልም፥ “እነሆ፥ ሕዝቡ ከደሙ ጋር በመብላታቸው እግዚአብሔርን በደሉ” ብለው ነገሩት። ሳኦልም በጌቴም “ትልቅ ድንጋይ አንከባልላችሁ አቅርቡልኝ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ለሳኦል፣ “እነሆ፤ ሕዝቡ ሥጋውን ከነደሙ በመብላት እግዚአብሔርን እየበደለ ነው” ተብሎ ተነገረው። ሳኦልም፣ “ሕግ ተላልፋችኋል፤ በሉ አንድ ትልቅ ድንጋይ አንከባላችሁ አቅርቡልኝ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ለሳኦል፥ “እነሆ፤ ሕዝቡ ሥጋውን ከነደሙ በመብላት ጌታን እየበደለ ነው” ተብሎ ተነገረው። ሳኦልም፥ “ይህ የክሕደት ተግባር ነው! አንድ ትልቅ ድንጋይ አንከባላችሁ ወደዚህ አምጡልኝ” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሳኦልም “ተመልከት ሕዝቡ ደም ያለበትን ሥጋ በመብላታቸው በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት ሠርተዋል” የሚል ወሬ ደረሰው። ሳኦልም “ይህ የክሕደት ተግባር ነው! አንድ ትልቅ ድንጋይ አንከባላችሁ ወደዚህ አምጡልኝ” ሲል ጮኸባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሳኦልም፦ እነሆ፥ ሕዝቡ ከደሙ ጋር በመብላታቸው እግዚአብሔርን በደሉ ብለው ነገሩት። ሳኦልም፦ እጅግ ተላለፋችሁ፥ አሁንም ትልቅ ድንጋይ አንከባልላችሁ አቅርቡልኝ አላቸው። |
“ከእስራኤልም ልጆች፥ ወይም በመካከላቸው ከሚኖሩ እንግዶች ማናቸውም ሰው ደም ቢበላ፥ ደም በሚበላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብድበታለሁ፤ ያንም ሰው ከሕዝቡ ለይች አጠፋዋለሁ።
ነገር ግን ለጣዖት ከሚሠዋው፥ ከዝሙት፥ ሞቶ የተገኘውንና ደም ከመብላት እንዲርቁ፥ ለራሳቸው የሚጠሉትንም በወንድሞቻቸው ላይ እንዳያደርጉ እዘዙአቸው።
አንተ ሰው ሆይ፥ እውነት ለሚፈርደው ለእግዚአብሔር ምን ትመልስለታለህ? በወንድምህ ላይ የምትጠላውን ያን ሥራ አንተ ራስህ ከሠራኸው በራስህ የምትፈርድ አይደለምን? አንተ ራስህ ያን ሥራ ትሠራዋለህና።
ሳኦልም፥ “በሕዝቡ መካከል እየዞራችሁ፦ እያንዳንዱ ሰው በሬውንና በጉን ወደ እኔ ያቅርብ፥ በዚህም እረዱና ብሉ፤ ከደሙም ጋር በመብላታችሁ እግዚአብሔርን አትበድሉ” በሉአቸው አለ። እያንዳንዱም ሰው ሁሉ በእጁ ያለውን በዚያች ሌሊት አቀረበ፤ በዚያም አረደው።