1 ሳሙኤል 12:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም የመረጣችሁትን ንጉሥ እዩ፤ እነሆም፥ እግዚአብሔር ንጉሥ ሰጣችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም የጠየቃችሁትና የመረጣችሁት ንጉሥ ይኸው፤ እነሆ፣ እግዚአብሔር በላያችሁ ንጉሥ አንግሧል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም የጠየቃችሁትና የመረጣችሁት ንጉሥ ይኸው፤ እነሆ፥ ጌታ በላያችሁ አነገሠላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የጠየቃችሁትንና የመረጣችሁትን ንጉሥ እነሆ እግዚአብሔር አነገሠላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም የመረጣችሁትንና የፈለጋችሁትን ንጉሥ እዩ፥ እነሆም፥ እግዚአብሔር ንጉሥ አደረገላችሁ። |
ከዚያም ወዲያ ንጉሥ ያነግሥላቸው ዘንድ ለመኑ፤ እግዚአብሔርም ከብንያም ነገድ የተወለደውን ሰው የቂስን ልጅ ሳኦልን አርባ ዓመት አነገሠላቸው።
ሳሙኤልም ለሕዝቡ ሁሉ፥ “ከሕዝቡ ሁሉ እርሱን የሚመስል እንደ ሌለ እግዚአብሔር የመረጠውን ታያላችሁን?” አላቸው፤ ሕዝቡም ሁሉ፥ “ንጉሥ ሕያው ይሁን” እያሉ እልልታ አደረጉ።
ሕዝቡም ሁሉ ወደ ጌልገላ ሄዱ፤ ሳሙኤልም ሳኦልን ቀብቶ በእግዚአብሔር ፊት በጌልጌላ አነገሠው፤ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት የእህል ቍርባንና የሰላም መሥዋዕት አቀረበ፤ በዚያም ሳኦልና የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ታላቅ ደስታ አደረጉ።
የስንዴ መከር ዛሬ አይደለምን? ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ እርሱም ነጐድጓድንና ዝናብን ይልካል፤ እናንተም ንጉሥ በመለመናችሁ በእግዚአብሔር ፊት ያደረጋችሁት ክፋት ታላቅ እንደ ሆነ ታውቃላችሁ፤ ታያላችሁም።”
ሕዝቡም ሁሉ ሳሙኤልን፥ “ንጉሥ በመለመናችን በኀጢአታችን ሁሉ ላይ ይህን ክፋት ጨምረናልና እንዳንሞት ስለ ባሪያዎችህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን” አሉት።
እንዲህም አሉት፥ “እነሆ፥ አንተ ሸምግለሃል፤ ልጆችህም በመንገድህ አይሄዱም፤ አሁንም እንደ ሌሎች አሕዛብ ሁሉ የሚፈርድልን ንጉሥ አንግሥልን።”
ከሦስት ቀንም በፊት የጠፉ አህዮችህ ተገኝተዋልና ልብህን አታስጨንቀው። የእስራኤል መልካም ምኞት ለማን ነው? ለአንተና ለአባትህ ቤት አይደለምን?” አለው።