Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ሳሙኤል 12:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 አሁንም የጠየቃችሁትና የመረጣችሁት ንጉሥ ይኸው፤ እነሆ፣ እግዚአብሔር በላያችሁ ንጉሥ አንግሧል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 አሁንም የጠየቃችሁትና የመረጣችሁት ንጉሥ ይኸው፤ እነሆ፥ ጌታ በላያችሁ አነገሠላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 “የጠየቃችሁትንና የመረጣችሁትን ንጉሥ እነሆ እግዚአብሔር አነገሠላችሁ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 አሁ​ንም የመ​ረ​ጣ​ች​ሁ​ትን ንጉሥ እዩ፤ እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጉሥ ሰጣ​ችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 አሁንም የመረጣችሁትንና የፈለጋችሁትን ንጉሥ እዩ፥ እነሆም፥ እግዚአብሔር ንጉሥ አደረገላችሁ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 12:13
9 Referencias Cruzadas  

በቍጣዬ ንጉሥን ሰጠሁህ፤ በመዓቴም ሻርሁት።


ሳሙኤልም መላውን ሕዝብ፣ “እግዚአብሔር የመረጠውን ሰው አያችሁን? ከሕዝቡ ሁሉ የሚስተካከለው ማንም የለም” አለ። ከዚያም ሕዝቡ፣ “ንጉሡ ለዘላለም ይኑር!” ብሎ ጮኸ።


እነርሱም፣ “አንተ አርጅተሃል፤ ልጆችህ ያንተን ፈለግ አይከተሉም፤ ስለዚህ ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት ሁሉ የሚመራን ንጉሥ አንግሥልን” አሉት።


ከዚያም ሕዝቡ ንጉሥ እንዲያነግሥላቸው ለመኑት፤ እግዚአብሔርም ከብንያም ወገን፣ የቂስን ልጅ ሳኦልን ሰጣቸው፤ እርሱም አርባ ዓመት ገዛቸው።


ሕዝቡ ሁሉ ወደ ጌልገላ ሄደ፤ የሳኦልንም ንጉሥነት በእግዚአብሔር ፊት አጸና። በዚያም ሕዝቡ የኅብረት መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት አቀረበ፤ ሳኦልና እስራኤላውያንም ሁሉ ታላቅ በዓል አደረጉ።


ከሦስት ቀን በፊት ስለ ጠፉብህ አህዮች አትጨነቅ፤ ተገኝተዋልና። የእስራኤል ምኞት ሁሉ ያዘነበለው ወደ አንተና ወደ አባትህ ቤተ ሰብ ሁሉ አይደለምን?”


አሁን የስንዴ መከር ጊዜ አይደለምን? እኔ ነጐድጓድና ዝናብ እንዲልክ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ እናንተም ንጉሥ እንዲነግሥላችሁ በመጠየቃችሁ በእግዚአብሔር ፊት የቱን ያህል የከፋ ድርጊት እንደፈጸማችሁ ያን ጊዜ ታውቃላችሁ።”


ሕዝቡም ሁሉ ሳሙኤልን፣ “ሌላው በደላችን ሳያንስ፣ ንጉሥ እንዲነግሥልን በመጠየቃችን ተጨማሪ ክፋት ስላደረግን እንዳንሞት፣ ለአገልጋዮችህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን” አሉት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios