1 ነገሥት 5:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እግዚአብሔር ከእግሩ በታች እስኪጥልለት ድረስ በዙሪያው ስለ ነበረ ጦርነት አባቴ ዳዊት ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ስም ቤት መሥራት እንዳልቻለ አንተ ታውቃለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አባቴ ዳዊት በዙሪያው ሁሉ ከገጠመው ጦርነት የተነሣ፣ እግዚአብሔር ጠላቶቹን ከእግሩ በታች እስኪጥልለት ድረስ ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስ መሥራት እንዳልቻለ ታውቃለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አባቴ ዳዊት በዙሪያው ከነበሩት የጠላት አገሮች ሠራዊት ጋር ሲዋጋ መኖሩን አንተ ራስህ ታውቀዋለህ፤ በጠላቶቹ ላይ ጌታ ድልን እስኪያጐናጽፈው ድረስ ለእግዚአብሔር ለጌታው ቤተ መቅደስ ለመሥራት አለመቻሉንም ታስታውሳለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አባቴ ዳዊት በዙሪያው ከነበሩት የጠላት አገሮች ሠራዊት ጋር ሲዋጋ መኖሩን አንተ ራስህ ታውቀዋለህ፤ በጠላቶቹ ላይ ድልን እስኪያጐናጽፈው ድረስ ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ለመሥራት አለመቻሉንም ታስታውሳለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “እግዚአብሔር ከእግሩ በታች እስኪጥልለት ድረስ በዙሪያው ስለ ነበረ ሰልፍ አባቴ ዳዊት የአምላኩን የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት እንዳልቻለ አንተ ታውቃለህ። |
ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ እጅግ ብዙ ደም አፍስሰሃል፤ ታላቅም ሰልፍ አድርገሃል፤ በፊቴም በምድር ላይ ብዙ ደም አፍስሰሃልና ለስሜ ቤት አትሠራም።
ንጉሡም ዳዊት በጉባኤው መካከል ቆሞ እንዲህ አለ፥ “ወንድሞቼና ሕዝቤ ሆይ፥ ስሙኝ፤ ለእግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ታቦትና ለአምላካችን እግር ማረፊያ የዕረፍት ቤት ለመሥራት አሳብ በልቤ መጣብኝ፤ ለዚህም ሥራ የሚያስፈልገውን አዘጋጅቻለሁ፤
የማዕዱንም መብል፥ የብላቴኖቹንም አቀማመጥ፥ የሎሌዎቹንም ሥርዐት፥ አለባበሳቸውንም፥ ጠጅ አሳላፊዎቹንም፥ አለባበሳቸውንም፥ በእግዚአብሔርም ቤት የሚያሳርገውን መሥዋዕት ባየች ጊዜ ተደነቀች።
ለአንድ ቀን አንድ በሬና ስድስት የሰቡ በጎች፥ አንድ ፍየልም፥ በዐሥር በዐሥር ቀንም ብዙ ልዩ ልዩ ዓይነት ወይን ጠጅ ይዘጋጅልኝ ነበር፤ ነገር ግን አገዛዝ በሕዝቡ ላይ ከብዶ ነበርና ለአለቃ የሚገባውን ቀለብ አልሻም ነበር።
እነዚያንም ነገሥት ወደ ኢያሱ ባመጡአቸው ጊዜ ኢያሱ የእስራኤልን ሰዎች ሁሉ ጠራ፤ ከእርሱም ጋር የሄዱትን የተዋጊዎችን አለቆች “ቅረቡ፤ በእነዚህም ነገሥት አንገት ላይ እግራችሁን አኑሩ” አላቸው። ቀረቡም በአንገታቸውም ላይ እግራቸውን አኖሩ።