አኪያልም የቤት አዛዥ፥ ኤልያቅም የቤት አዛዦች አለቃ ነበረ፥ የሳፋን ልጅ ኤልያፍም የቤተ ሰብ ሐላፊ፥ የአዶን ልጅ አዶኒራምም ግብር አስገባሪ ነበረ።
1 ነገሥት 5:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም ከእስራኤል ሁሉ ገባሮቹን መርጦ አወጣ፤ የገባሮቹም ቍጥር ሠላሳ ሺህ ሰዎች ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ ሰሎሞን ከመላው እስራኤል የጕልበት ሠራተኞችን መለመለ፤ ቍጥራቸውም ሠላሳ ሺሕ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሥ ሰሎሞን ከመላው እስራኤል ሠላሳ ሺህ የግዳጅ ሠራተኞችን መለመለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሰሎሞን ከመላው እስራኤል ሠላሳ ሺህ የግዳጅ ሠራተኞችን መለመለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም ከእስራኤል ሁሉ ገባሮቹን መርጦ አወጣ፤ የገባሮቹም ቍጥር ሠላሳ ሺህ ሰዎች ነበረ። |
አኪያልም የቤት አዛዥ፥ ኤልያቅም የቤት አዛዦች አለቃ ነበረ፥ የሳፋን ልጅ ኤልያፍም የቤተ ሰብ ሐላፊ፥ የአዶን ልጅ አዶኒራምም ግብር አስገባሪ ነበረ።
ንጉሡም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤትና ቤተ መንግሥቱን፥ ሜሎንንም፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር፥ አሶርንም፥ መጊዶንም፥ ጋዜርንም ይሠራ ዘንድ ሠራተኞችን መልምሎ ነበር።
“አባትህ ቀንበር አክብዶብን ነበር፤ አሁንም አንተ ጽኑውን የአባትህን አገዛዝ፥ በላያችንም የጫነውን የከበደውን ቀንበር አቅልልልን፥ እኛም እንገዛልሃለን።”
የእስራኤልም ልጆች ያላጠፉአቸውን፥ በኋላቸውም በምድር ላይ የቀሩትን ልጆቻቸውን ሰሎሞን እስከ ዛሬ ድረስ ገባሮች አደረጋቸው።