Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 5:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ነገ​ረው ለሰ​ሎ​ሞን ጥበ​ብን ሰጠው፤ በኪ​ራ​ምና በሰ​ሎ​ሞ​ንም መካ​ከል ሰላም ነበረ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ቃል ኪዳን አደ​ረጉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እግዚአብሔርም በገባለት ተስፋ መሠረት ለሰሎሞን ጥበብን ሰጠው፤ በኪራምና በሰሎሞን መካከልም መልካም ግንኙነት ነበር፤ ሁለቱም ቃል ኪዳን አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ጌታ አስቀድሞ የሰጠውን የተስፋ ቃል በመጠበቅ ለሰሎሞን ጥበብን ሰጠው፤ በኪራምና በሰሎሞን መካከል ሰላም ስለ ነበረ ሁለቱም የጋራ ስምምነት ውል አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እግዚአብሔር አስቀድሞ የሰጠውን የተስፋ ቃል በመጠበቅ ለሰሎሞን ጥበብን ሰጠው፤ በኪራምና በሰሎሞን መካከል ሰላም ስለ ነበረ ሁለቱም የጋራ ስምምነት ውል አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እግዚአብሔርም እንደ ነገረው ለሰሎሞን ጥበብን ሰጠው፤ በኪራምና በሰሎሞንም መካከል ሰላም ነበረ፤ ሁለቱም ቃል ኪዳን ተጋቡ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 5:12
12 Referencias Cruzadas  

በዐ​ዘ​ቅተ መሐላ አጠ​ገ​ብም ቃል ኪዳ​ንን አደ​ረጉ። አቤ​ሜ​ሌ​ክና ሚዜው አኮ​ዞት፥ የሠ​ራ​ዊቱ አለቃ ፋኮ​ልም ተነ​ሥ​ተው ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ምድር ተመ​ለሱ።


“በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል በአ​ባ​ቴና በአ​ባ​ትህ መካ​ከል ቃል ኪዳን ጸን​ቶ​አል፤ እነሆ፥ ብርና ወርቅ ገጸ በረ​ከት ልኬ​ል​ሃ​ለሁ፤ እርሱ ከእኔ ዘንድ እን​ዲ​ርቅ ሄደህ ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ከባ​ኦስ ጋር ያለ​ህን ቃል ኪዳን አፍ​ርስ” ብሎ ላከ።


እነሆ፥ እኔ እንደ ቃልህ አድ​ር​ጌ​ል​ሃ​ለሁ፤ እነ​ሆም፥ ማንም የሚ​መ​ስ​ልህ ከአ​ንተ በፊት እን​ደ​ሌለ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ እን​ዳ​ይ​ነሣ አድ​ርጌ ጥበ​በ​ኛና አስ​ተ​ዋይ ልቡና ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሰ​ሎ​ሞን እጅግ ብዙ ጥበ​ብ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን፥ በባ​ሕ​ርም ዳር እን​ዳለ አሸዋ የልብ ስፋ​ትን ሰጠው።


ሰሎ​ሞ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ገባ​ሮ​ቹን መርጦ አወጣ፤ የገ​ባ​ሮ​ቹም ቍጥር ሠላሳ ሺህ ሰዎች ነበረ።


ጥበ​ብ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ። ካንተ በፊት ለነ​በሩ ነገ​ሥ​ታት ያል​ተ​ሰ​ጠ​ውን፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ለሚ​ነሡ የማ​ይ​ሰ​ጠ​ውን ብል​ፅ​ግ​ናን፥ ገን​ዘ​ብ​ንና ክብ​ርን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ሩት ሁሉ፥ በመ​ን​ገ​ዶ​ቹም የሚ​ሄዱ ብፁ​ዓን ናቸው።


ለእስራኤል የነገሠ የዳዊት ልጅ የሰሎሞን ምሳሌዎች፤


ሰባ​ኪ​ውም ጠቢብ ስለ ሆነ ለሕ​ዝቡ ዕው​ቀ​ትን አስ​ተ​ማረ፥ ጆሮ​ውም እን​ቆ​ቅ​ል​ሽን መረ​መረ።


ከመ​ዝ​ሙር ሁሉ የሚ​በ​ልጥ የሰ​ሎ​ሞን መዝ​ሙር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የሰ​ሎ​ሞን ምር​ኮ​ኞ​ችን በኤ​ዶ​ም​ያስ ዘግ​ተ​ዋ​ልና፥ የወ​ን​ድ​ሞ​ች​ንም ቃል ኪዳን አላ​ሰ​ቡ​ምና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጢ​ሮስ ኀጢ​አት አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።


ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፤ ለእርሱም ይሰጠዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos