1 ነገሥት 22:52 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ፤ በአባቱ በአክዓብ፥ በእናቱም በኤልዛቤል መንገድ፥ እስራኤልንም ባሳተው በናባጥ ልጅ በኢዮርብዓም መንገድ ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም የአባቱንና የእናቱን፣ እንዲሁም እስራኤልን ያሳተውን የናባጥን ልጅ የኢዮርብዓምን መንገድ በመከተሉ፣ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ክፉ ሥራ ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ በነገሠ በዐሥራ ሰባተኛው ዓመት የአክዓብ ልጅ አካዝያስ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ መኖሪያውንም በሰማርያ አድርጎ ሁለት ዓመት ገዛ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም የአባቱን የአክዓብን፥ የእናቱን የኤልዛቤልንና የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ኃጢአት የመራውን የንጉሥ ኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት በመከተል በእግዚአብሔር ፊት በደል ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ፤ በአባቱና በእናቱም መንገድ፥ እስራኤልንም ባሳተው በናባጥ ልጅ በኢዮርብዓም መንገድ ሄደ። |
በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ፥ በናባጥም ልጅ በኢዮርብዓም መንገድ እስራኤልንም ባሳተበት ኀጢአት ሄደ።
ሌሎች ሠራዊትን እናመጣልሃለን፤ አንተም ቀድሞ በሞቱብህ ሠራዊት ምትክ ሹም፤ ፈረሱን በፈረስ ፋንታ፥ ሰረገላውን በሰረገላ ፋንታ ለውጥ፤ በሜዳውም እንዋጋቸዋለን፤ ድልም እናደርጋቸዋለን።” እርሱም ምክራቸውን ሰማ፤ እንዲሁም አደረገ።
ኢዮራምም ኢዩን ባየ ጊዜ “ኢዩ ሆይ፥ ሰላም ነውን?” አለ። እርሱም፥ “የእናትህ የኤልዛቤል ግልሙትናዋና መተቷ ሲበዛ ምን ሰላም አለ?” ብሎ መለሰ።
እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ፤ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ፤ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።