2 ነገሥት 9:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ኢዮራምም ኢዩን ባየ ጊዜ “ኢዩ ሆይ፥ ሰላም ነውን?” አለ። እርሱም፥ “የእናትህ የኤልዛቤል ግልሙትናዋና መተቷ ሲበዛ ምን ሰላም አለ?” ብሎ መለሰ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ኢዮራምም ኢዩን ገና ሲያየው፣ “ኢዩ፣ የመጣኸው በሰላም ነውን?” ሲል ጠየቀው። ኢዩም፣ “የእናትህ የኤልዛቤል የጣዖት አምልኮና መተት እንዲህ በዝቶ እያለ ምን ሰላም አለ!” ሲል መለሰ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ኢዮራምም “ኢዩ ሆይ፥ አመጣጥህ በሰላም ነውን?” ሲል ጠየቀ። ኢዩም፦ “እናትህ ኤልዛቤል ባመጣችው አስማትና የጣዖት አምልኮ ውስጥ ተነክረን እስካለን ድረስ ምን ሰላም አለ?” ሲል መለሰለት። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ኢዮራምም “ኢዩ ሆይ፥ አመጣጥህ በሰላም ነውን?” ሲል ጠየቀ። ኢዩም፦ “እናትህ ኤልዛቤል ባመጣችው አስማትና የጣዖት አምልኮ ውስጥ ተነክረን እስካለን ድረስ ምን ሰላም አለ?” ሲል መለሰለት። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ኢዮራምም ኢዩን ባየ ጊዜ “ኢዩ ሆይ! ሰላም ነውን?” አለ። እርሱም “የእናትህ የኤልዛቤል ግልሙትናዋና መተትዋ ሲበዛ ምን ሰላም አለ?” ብሎ መለሰ። Ver Capítulo |