1 ነገሥት 19:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተነሥቶም በላ፤ ጠጣም፤ በዚያም በበላው የምግብ ኀይል እስከ ኮሬብ ድረስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ተነሥቶ በላ፤ ጠጣም፤ በምግቡም ብርታት አግኝቶ ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወደ ኮሬብ እስኪደርስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ተጓዘ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልያስም ተነሥቶ ምግቡን በላ፥ ውሃውንም ጠጣ፤ ከዚያም ምግብ ባገኘው ኃይል እስከ ተቀደሰው የሲና ተራራ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሙሉ ተጓዘ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልያስም ተነሥቶ ምግቡን በላ፥ ውሃውንም ጠጣ፤ ከዚያም ምግብ ባገኘው ኀይል እስከ ተቀደሰው የሲና ተራራ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሙሉ ተጓዘ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተነሥቶም በላ፤ ጠጣም፤ በዚያም ምግብ ኀይል እስከ እግዚአብሔር ተራራ እስከ ኮሬብ ድረስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሄደ። |
የእግዚአብሔር መልአክ ደግሞ ሁለተኛ ጊዜ መጥቶ ዳሰሰውና፥ “የምትሄድበት መንገድ ሩቅ ነውና ተነሥተህ ብላ” አለው።
እግዚአብሔርም በእሳት ስለ ወረደበት የሲና ተራራ ሁሉ እንደ ምድጃ ጢስ ይጤስ ነበር፤ ከእርሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ተራራውም ሁሉ እጅግ ይናወጥ ነበር፤ ሕዝቡም ፈጽመው ደነገጡ።
ሙሴም የአማቱን የምድያምን ካህን የዮቶርን በጎች ይጠብቅ ነበር፤ በጎቹንም ወደ ምድረ በዳ ዳርቻ ነዳ፤ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ።
በዚያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በእግዚአብሔር ፊት ነበረ፤ እንጀራም አልበላም፤ ውኃም አልጠጣም። በጽላቱም ዐሥሩን የቃል ኪዳን ቃሎች ጻፈ።
እግዚአብሔርም አሮንን አለው፥ “ሄደህ በምድረ በዳ ሙሴን ተገናኘው፤” ሄዶም በእግዚአብሔር ተራራ ተገናኘው፤ እርስ በርሳቸውም ተሳሳሙ።
አርባ መዓልትና አርባ ሌሊት ከዲያብሎስ ተፈተነ፥ በእነዚያም ቀኖች ምንም አልበላም፤ እነዚያም ቀኖች ከተፈጸሙ በኋላ ተራበ።
እርሱም፥ “ጸጋዬ ይበቃሀል፤ ኀይልስ በደዌ ያልቃል” አለኝ፤ የክርስቶስም ኀይል በእኔ ላይ ያድር ዘንድ በመከራዬ ልመካ ወደድሁ።
ስለ ሠራችሁት ኀጢአት ሁሉ፥ እርሱንም ለማስቈጣት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ስላደረጋችሁ፥ እንደ ፊተኛው በእግዚአብሔር ፊት አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ዳግመኛ ለመንሁ፤ እንጀራ አልበላሁም፥ ውኃም አልጠጣሁም።