እርሱም፥ “በብላቴናው ላይ እጅህን አትዘርጋ፤ አንዳችም አታድርግበት፤ ለምትውድደው ልጅህ ከእኔ አልራራህለትምና አንተ እግዚአብሔርን የምትፈራ እንደሆንህ አሁን ዐውቄአለሁ” አለው።
1 ነገሥት 18:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አክዓብም የቤቱን አዛዢ አብድዩን ጠራ፤ አብድዩም እግዚአብሔርን እጅግ ይፈራ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አክዓብም የቤተ መንግሥቱን አዛዥ አብድዩን ጠራው፤ አብድዩም እግዚአብሔርን በጣም የሚፈራ ሰው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ንጉሥ አክዓብ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ የሆነውን አብድዩን ጠራ፤ አብድዩ ጌታን የሚፈራ መንፈሳዊ ሰው ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ንጉሥ አክዓብ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ የሆነውን አብድዩን ጠራ፤ አብድዩ እግዚአብሔርን የሚፈራ መንፈሳዊ ሰው ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አክዓብም የቤቱን አዛዥ አብድዩን ጠራ፤ አብድዩ እግዚአብሔርን እጅግ ይፈራ ነበር። |
እርሱም፥ “በብላቴናው ላይ እጅህን አትዘርጋ፤ አንዳችም አታድርግበት፤ ለምትውድደው ልጅህ ከእኔ አልራራህለትምና አንተ እግዚአብሔርን የምትፈራ እንደሆንህ አሁን ዐውቄአለሁ” አለው።
ሎሌውም ከጌታው ግመሎች መካከል ዐሥር ግመሎችን ወስዶ፥ ከጌታውም ዕቃ መልካም መልካሙን ይዞ ተነሣ፤ ተነሥቶም ወደ ሦርያ ወንዞች መካከል ወደ ናኮር ከተማ ሄደ።
በዚህ ቤት ከእኔ የሚበልጥ ሰው የለም፤ ሚስቱ ስለሆንሽ ከአንቺ በቀር ያልሰጠኝ ነገር የለም፤ እንዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደርጋለሁ? በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኀጢአትን እሠራለሁ?”
የእኩሌቶቹ ፈረሶች አለቃ ዘምሪም አሽከሮቹን ሁሉ ሰብስቦ ዐመፀ፤ ኤላም በቴርሳ ነበረ፤ በቴርሳም በነበረው በመጋቢው በአሳ ቤት ይሰክር ነበር።
እኔም ከአንተ ጥቂት ራቅ ስል የእግዚአብሔር መንፈስ አንሥቶ ወደማላውቀው ስፍራ ይወስድሃል፤ እኔም ገብቼ ለአክዓብ ስናገር፥ ባያገኝህ ይገድለኛል፤ እኔም ባሪያህ ከትንሽነቴ ጀምሬ እግዚአብሔርን እፈራ ነበር።
ከነቢያትም ልጆች የአንዱ ሚስት የሆነች አንዲት ሴት፥ “ባሌ ባሪያህ ሞቶአል፤ ባሪያህም እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንደ ነበረ አንተ ታውቃለህ፤ ባለ ዕዳም ሁለቱ ልጆቼን ባሪያዎች አድርጎ ሊወስዳቸው መጥቶአል” ብላ ወደ ኤልሳዕ ጮኸች።
ከእኔ አስቀድመው የነበሩት አለቆች ግን በሕዝቡ ላይ አክብደው ነበር፤ ስለ እንጀራውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወስዱ ነበር፤ ሎሌዎቻቸውም ደግሞ በሕዝቡ ላይ ይሰለጥኑ ነበር። እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለ ፈራሁ እንዲህ አላደረግሁም።
ወንድሜን ሃናኒንና የግንቡን አለቃ ሐናንያንም በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኋቸው፤ እርሱም እውነተኛ ከሌሎቹም ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ።
የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈሩ እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩ፣ እግዚአብሔርም አደመጠ፥ ሰማም፥ እግዚአብሔርንም ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ የመታሰቢያ መጽሐፍ በፊቱ ተጻፈ።
እርሱም ጻድቅና ከነቤተ ሰቡ እግዚአብሔርን የሚፈራ ነበር፤ ለሕዝቡም ብዙ ምጽዋት ይሰጥ ነበር፤ ዘወትርም ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ነበር።