La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ነገሥት 14:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሂጂ ለኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም እን​ዲህ በዪው፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከሕ​ዝብ መካ​ከል ለይቼ ከፍ አድ​ር​ጌህ ነበር፤ በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይም ንጉሥ አድ​ር​ጌህ ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አሁንም ሂጂና ኢዮርብዓምን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው ብለሽ ንገሪው፤ ‘ከሕዝቡ መካከል አንሥቼ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግሁህ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ ኢዮርብዓም ሂጂ፤ የእስራኤል አምላክ ጌታ የሚለውን ንገሪው፤ ቃሉም ይህ ነው፤ ‘ከሕዝብ መካከል መርጬ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግኹህ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወደ ኢዮርብዓም ሂጂ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለውን ንገሪው፤ ቃሉም ይህ ነው፤ ‘ከሕዝብ መካከል መርጬ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግኹህ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሂጂ፤ ለኢዮርብዓምም እንዲህ በዪው ‘የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከሕዝብ መካከል ለይቼ ከፍ አድርጌህ ነበር፤ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ አለቃ አድርጌህ ነበር፤

Ver Capítulo



1 ነገሥት 14:7
11 Referencias Cruzadas  

ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ጽኑዕ ኀያል ሰው ነበረ፤ ሰሎ​ሞ​ንም ጐል​ማ​ሳው ኢዮ​ር​ብ​ዓም በሥራ የጸና መሆ​ኑን ባየ ጊዜ በዮ​ሴፍ ነገድ ሥራ ሁሉ ላይ ሾመው።


መን​ግ​ሥ​ቱ​ንም ከልጁ እጅ እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ለአ​ን​ተም ዐሥ​ሩን ነገድ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


አን​ተ​ንም እወ​ስ​ድ​ሃ​ለሁ፤ ነፍ​ስ​ህም በወ​ደ​ደ​ችው ሁሉ ላይ አነ​ግ​ሥ​ሃ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ንጉሥ ትሆ​ና​ለህ።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ይህ ነገር ከእኔ ዘንድ ነውና አት​ውጡ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን አት​ውጉ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ ቤቱ ይመ​ለስ።” እነ​ር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰሙ፤ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ተመ​ል​ሰው ሄዱ።


ይህም ነገር ከገጸ ምድር ለመ​ፍ​ረ​ስና ለመ​ጥ​ፋት በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት ላይ ኀጢ​አት ሆነ።


እር​ስ​ዋም በደጅ ስት​ገባ አኪያ የእ​ግ​ር​ዋን ኮቴ ሰማ፤ እን​ዲ​ህም አላት፥ “የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ሚስት ሆይ፥ ግቢ! ስለ​ም​ንስ ራስ​ሽን ለወ​ጥሽ? እኔም የሚ​ያ​ስ​ጨ​ንቅ ወሬ ይዤ ወደ አንቺ ተል​ኬ​አ​ለሁ።


“እኔ ከመ​ሬት አን​ሥቼ በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ አንተ ግን በከ​ንቱ ጣዖ​ታ​ቸው ያስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን በአ​ሳ​ታ​ቸው በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም መን​ገድ ሄድህ፤


በቍ​ጣዬ ንጉ​ሥን ሰጠ​ሁህ፤ በመ​ዓ​ቴም ሻር​ሁት።


ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን፥ “ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ሌሊት የነ​ገ​ረ​ኝን ልን​ገ​ርህ” አለው፤ እር​ሱም፥ “ተና​ገር” አለው።