1 ነገሥት 10:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሳባም ንግሥት የሰሎሞንን ስም፥ የእግዚአብሔርንም ስም በሰማች ጊዜ ሰሎሞንን በእንቆቅልሽ ትፈትነው ዘንድ መጣች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሳባ ንግሥት የሰሎሞንን ዝና እና ከእግዚአብሔር ስም ጋራ ያለውን ግንኙነት በሰማች ጊዜ፣ አስቸጋሪ በሆኑ ጥያቄዎች ልትፈትነው መጣች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንግሥተ ሳባ እግዚአብሔር ለሰሎሞን ስለ ሰጠው አስደናቂ ጥበብ የሚነገረውን ሁሉ ሰማች፤ ስለዚህ አስቸጋሪ በሆኑ ከባድ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንግሥተ ሳባ እግዚአብሔር ለሰሎሞን ስለ ሰጠው አስደናቂ ጥበብ የሚነገረውን ሁሉ ሰማች፤ ስለዚህ አስቸጋሪ በሆኑ ከባድ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሳባም ንግሥት በእግዚአብሔር ስም የወጣለትን የሰሎሞንን ዝና በሰማች ጊዜ በእንቆቅልሽ ትፈትነው ዘንድ መጣች። |
ከሰዎችም ሁሉ ይልቅ ብልህ ነበረ፤ ከኢይዝራኤላዊው ከኤታንና ከማሖል ልጆች ከአውናንና ከከልቀድ፥ ከደራልም ይልቅ ጥበበኛ ነበረ። በዙሪያውም ባሉ አሕዛብ ሁሉ ዝናው ወጣ።
በየወሩም እያፈራረቀ ወደ ሊባኖስ ዐሥር ዐሥር ሺህ ይልክ ነበር፤ አንድ ወርም በሊባኖስ፥ ሁለት ወርም በቤታቸው ይቀመጡ ነበር። አዶኒራምም የገባሪዎች አለቃ ነበረ።
የግመሎች መንጋ ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የምድያምና የኤፋ ግመሎች ይሸፍኑሻል፤ ሁሉ ከሳባ ወርቅንና ዕጣንን ይዘው ይመጣሉ፤ የእግዚአብሔርንም ማዳን ያበሥራሉ።
ስለ ምንስ ከሳባ ዕጣንን፥ ከሩቅም ሀገር ቀረፋን ታቀርቡልኛላችሁ? የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን አልቀበለውም፤ ቍርባናችሁም ደስ አያሰኘኝም።
ባንቺ ላይ ከአኖርኋት ከክብሬ የተነሣ ውበትሽ ፍጹም ነበረና ስምሽ በአሕዛብ መካከል ተሰማ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ሳባና ድዳን፥ የተርሴስም ነጋዴዎች፥ መንደሮችዋም ሁሉ፦ ምርኮን ትማርክ ዘንድ መጥተሃልን? ብዝበዛንስ ትበዘብዝ ዘንድ፥ ብርንና ወርቅንስ ትወስድ ዘንድ፥ ከብትንና ዕቃንስ ትወስድ ዘንድ፥ እጅግስ ብዙ ምርኮ ትማርክ ዘንድ ወገንህን ሰብስበሃልን? ይሉሃል።”
ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፤ እነሆም ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ።
የአዜብ ንግሥት በፍርድ ቀን ከዚች ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፋረዳቸዋለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ልትሰማ ከምድር ዳርቻ መጥታለችና፤ እነሆ፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ በዚህ አለ።
ብቻህን እውነተኛ አምላክ የሆንህ አንተን፥ የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘለዓለም ሕይወት ናት።