የሳኦልም ልጅ የዮናታን ልጅ ሜምፌቡስቴ ወደ ዳዊት መጣ፤ በግንባሩም ወድቆ ሰገደለት፤ ንጉሥ ዳዊትም፥ “ሜምፌቡስቴ ሆይ፥” አለ፤ እርሱም፥ “እነሆኝ አገልጋይህ” አለ።
1 ነገሥት 1:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤርሳቤህም በግንባርዋ በምድር ላይ ተደፍታ ለንጉሡ ሰገደችና፥ “ጌታዬ ንጉሥ ዳዊት ለዘለዓለም በሕይወት ይኑር” አለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤርሳቤህም ለጥ ብላ እጅ ከነሣች በኋላ፣ በንጉሡ ፊት ተንበርክካ፣ “ጌታዬ ንጉሥ ዳዊት ለዘላለም ይኑር!” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤርሳቤህም በግምባርዋ በምድር ላይ ተደፍታ ለንጉሡ እጅ ነሣችና፦ “ጌታዬ ንጉሥ ዳዊት ለዘለዓለም በሕይወት ይኑር!” አለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቤርሳቤህም ወደ መሬት ለጥ ብላ እጅ በመንሣት “ጌታዬ ንጉሥ ዳዊት ለዘለዓለም በሕይወት ይኑር!” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤርሳቤህም በግምባርዋ በምድር ላይ ተደፍታ ለንጉሡ እጅ ነሣችና “ጌታዬ ንጉሥ ዳዊት ለዘላለም በሕይወት ይኑር!” አለች። |
የሳኦልም ልጅ የዮናታን ልጅ ሜምፌቡስቴ ወደ ዳዊት መጣ፤ በግንባሩም ወድቆ ሰገደለት፤ ንጉሥ ዳዊትም፥ “ሜምፌቡስቴ ሆይ፥” አለ፤ እርሱም፥ “እነሆኝ አገልጋይህ” አለ።
እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬዎችንና ጠቦቶችን፥ በጎችንም ሠውቶአል፤ የንጉሡንም ልጆች ሁሉ፥ የሠራዊቱን አለቃ ኢዮአብን፥ ካህኑንም አብያታርን ጠርቶአል፤ እነሆም፥ በፊቱ እየበሉና እየጠጡ፦ አዶንያስ ሺህ ዓመት ይንገሥ ይላሉ።
ንጉሡንም፥ “ንጉሡ ለዘለዓለም ይኑር፤ የአባቶች መቃብር ያለባት ከተማ ተፈትታለችና፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋልና ፊቴ ስለ ምን አያዝን?” አልሁት።
በሥጋ የወለዱን አባቶቻችን የሚቀጡን፥ እኛም የምንፈራቸው ከሆነ፥ እንግዲያ ይልቁን ለመንፈስ አባታችን ልንታዘዝና ልንገዛ በሕይወትም ልንኖር እንዴት ይገባን ይሆን?
ብላቴናውም በሄደ ጊዜ ዳዊት ከኤርገብ ተነሣ፤ በምድርም ላይ በግንባሩ ተደፋ፤ ሦስት ጊዜም ሰገደ፤ እርስ በእርሳቸውም ተሳሳሙ፤ ለረዥም ሰዓትም ተላቀሱ።
ዳዊትም በዚህ ቃል ሰዎቹን ከለከላቸው። በሳኦልም ላይ ተነሥተው ይገድሉት ዘንድ አልፈቀደላቸውም፤ ሳኦልም ከዋሻው ተነሥቶ መንገዱን ሄደ።