“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባቶችህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም ተገዛለት፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይተውሃል።
1 ቆሮንቶስ 9:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንስ በፈቃዴ አድርጌው ብሆን ዋጋዬን ባገኘሁ ነበር፤ በግድ ከሆነ ግን በተሰጠኝ መጋቢነት አገለገልሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በፈቃደኝነት ብሰብክ ሽልማት አለኝ፤ በፈቃደኝነት ካልሆነ ግን፣ የምፈጽመው ተግባር የተጣለብኝን ዐደራ መወጣት ብቻ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን በፈቃዴ ባደርገው ዋጋ አለኝና፤ ያለ ፈቃዴ ግን ባደርገው መጋቢነት በአደራ ተሰጥቶኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወንጌልን ቃል ያለ ግዴታ በፈቃዴ ባበሥር የድካም ዋጋ ይኖረኛል፤ በግዴታ ባደርገው ግን በዐደራ የተሰጠኝን ኀላፊነት ፈጸምኩ እንጂ ሌላ ያደረግኹት ነገር አለ ማለት አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህን በፈቃዴ ባደርገው ደመወዝ አለኝና፤ ያለ ፈቃዴ ግን ባደርገው መጋቢነት በአደራ ተሰጥቶኛል። |
“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባቶችህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም ተገዛለት፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይተውሃል።
ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና፥ ከእጅህም የተቀበልነውን ሰጥተንሃልና ይህን ያህል ችለን ልናቀርብልህ እኔ ማን ነኝ? ሕዝቤስ ማን ነው?
በሠራተኞች እጅ ለሚሠራው ሥራ ሁሉ ለወርቁ ዕቃ ወርቁን፥ ለብሩም ዕቃ ብሩን ሰጥቻለሁ። ዛሬ በዚች ቀን በፈቃዱ አገልግሎቱን ለእግዚአብሔር የሚፈጽም ማን ነው?”
ሕዝቡም ፈቅደው ሰጥተዋልና፥ በፍጹም ልባቸውም ለእግዚአብሔር በፈቃዳቸው አቅርበዋልና ደስ አላቸው፤ ንጉሡም ዳዊት ደግሞ ታላቅ ደስታ ደስ አለው።
የጌታንም ድምፅ፥ “ማንን እልካለሁ? ማንስ ወደዚያ ሕዝብ ይሄድልናል?” ሲል ሰማሁ? እኔም፥ “እነሆኝ፥ ጌታዬ፥ እኔን ላከኝ” አልሁ።
እኔም እንዲህ አልሁ፥ “የእግዚአብሔርን ስም አላነሣም፤ ከእንግዲህ ወዲህ በስሙ አልናገርም፥” በአጥንቶች ውስጥ እንደ ገባ እንደሚነድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነብኝ፤ ደከምሁ፤ መሸከምም አልቻልሁም።
ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ወደ ተርሴስ ይሸሽ ዘንድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮጴም ወረደ፤ ወደ ተርሴስም የምታልፍ መርከብ አገኘ፤ ከእግዚአብሔርም ፊት ኰብልሎ ከእነርሱ ጋር ወደ ተርሴስ ይሄድ ዘንድ ዋጋ ሰጥቶ ወደ እርስዋ ገባ።
በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ ዘንድ ደጅ የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥ ቍርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ጌታችንም እንዲህ አለው፥ “ምግባቸውን በየጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተሰቡ ላይ የሚሾመው ደግ ታማኝና ብልህ መጋቢ ማን ይሆን?
አጫጅም ዋጋውን ያገኛል፤ የሚዘራና የሚያጭድም በአንድነት ደስ እንዲላቸው ለዘለዓለም ሕይወት ፍሬን ይሰበስባል።
እንግዲህ ዋጋዬ ምንድን ነው? ወንጌልን ባስተምርም በሹመቴ የማገኘው ሳይኖር ወንጌልን ያለ ዋጋ እንዳስተምር ባደርግ ነው።
የጴጥሮስ ትምህርት በተገዘሩ በአይሁድ ዘንድ እንደ ታመነለት፥ የእኔም ትምህርት ባልተገዘሩ በአሕዛብ ዘንድ እንደ ታመነ ዐውቀዋል እንጂ።
ነገር ግን ወንጌልን አደራ ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔር የታመንን ሆነን እንዳገኘን መጠን፥ እንዲሁ እንናገራለን፤ ልባችንን የሚመረምር እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን ደስ እንደምናሰኝ አይደለም።