መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ በትእዛዜም እንድትሄዱ አደርጋችኋለሁ፤ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ።
1 ቆሮንቶስ 3:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ፥ የእግዚአብሔር መንፈስም በእናንተ ላይ አድሮ እንደሚኖር አታውቁምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ራሳችሁ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ፣ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውስጣችሁ እንደሚኖር አታውቁምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደሚኖርባችሁ አታውቁምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሆናችሁንና የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችሁ መኖሩን አታውቁምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? |
መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ በትእዛዜም እንድትሄዱ አደርጋችኋለሁ፤ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ።
እርሱም ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ እናንተ ግን ታውቁታላችሁ፤ በእናንተ ዘንድ ይኖራልና፤ ያድርባችሁማልና።
ለምትታዘዙለት፥ እሺ ለምትሉትም እናንተ አገልጋዮች እንደ ሆናችሁ አታውቁምን? ለተባበራችሁለትስ ራሳችሁን እንደ አስገዛችሁ አታውቁምን? ኀጢአትንም እሺ ብትሉአት፥ ተባብራችሁም ብትበድሉ እናንት ለሞት ተገዢዎች ትሆናላችሁ፤ ጽድቅንም እሺ ብትሉአት ለበጎ ሥራም ብትተባበሩ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናችሁ።
ጌታችን ኢየሱስን ከሙታን ለይቶ ያስነሣው የእግዚአብሔር መንፈስ ካደረባችሁ ኢየሱስ ክርስቶስን ከሙታን ለይቶ ያስነሣው እርሱ አድሮባችሁ ባለ መንፈሱ ለሟች ሰውነታችሁ ሕይወትን ይሰጣታል።
እናንተ ግን ለመንፈሳዊ ሕግ እንጂ ለሥጋችሁ ፈቃድ የምትሠሩ አይደላችሁም፤ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ አድሮ ይኖራልና፤ የክርስቶስ መንፈስ ያላደረበት ግን እርሱ የእርሱ ወገን አይደለም።
የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የሚያፈርሰውን ግን እርሱን ደግሞ እግዚአብሔር ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነውና፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም እናንተ ራሳችሁ ናችሁ፤ እንግዲያስ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ አታርክሱ።
በእግዚአብሔር ሥራ እንተባበራለንና፤ የእግዚአብሔርም አገልጋዮች ነንና፤ እናንተም የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ።
ከአመንዝራ ጋር የተገናኘ ከእርስዋ ጋር አንድ አካል እንዲሆን አታውቁምን? መጽሐፍ፥ “ሁለቱ አንድ አካል ይሆናሉ” ብሎአልና።
ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር ለተቀበላችሁት በእናንተ አድሮ ላለ ለመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? ለራሳችሁም አይደላችሁም።
ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? አያስቱአችሁ፤ ሴሰኞች፥ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ፥ ወይም አመንዝራዎች፥ ወይም ቀላጮች፥ ወይም በወንድ ላይ ዝሙትን የሚሠሩ፥ የሚሠሩባቸውም ቢሆኑ፤
የጣዖታቱ ካህናት የጣዖታቱን መባ እንደሚበሉ አታውቁምን? መሠዊያውን የሚያገለግሉም መሥዋዕቱን እንደሚካፈሉ አታውቁምን? ለቤተ እግዚአብሔር ሹሞች መተዳደሪያቸው የቤተ እግዚአብሔር መባ ነው።
በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሽቀዳደሙ ሁሉ እንደሚፋጠኑ አታውቁምን? ለቀደመው የሚደረግለት ዋጋ አለ፤ እንዲሁ እናንተም እንድታገኙ ፈጽማችሁ ሩጡ።
የእግዚአብሔርን ታቦትስ በጣዖት ቤት ውስጥ የሚያኖር ማን ነው? የሕያው እግዚአብሔር ማደሪያዎች እኛ አይደለንምን? እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረ፥ “እኔ በእነርሱ አድራለሁ፤ በመካከላቸውም እኖራለሁ፤ አምላካቸውም እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆኑኛል።”
ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።
ክርስቶስ ግን እንደ ልጅ በቤቱ ላይ የታመነ ነው፤ እኛም የምንደፍርበትን፥ የምንመካበትንም ተስፋ እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ ቤቱ ነን።
አመንዝሮች ሆይ! ዓለምን መውደድ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።
እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።