Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 6:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ሥጋ​ችሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁት በእ​ና​ንተ አድሮ ላለ ለመ​ን​ፈስ ቅዱስ ቤተ መቅ​ደስ እንደ ሆነ አታ​ው​ቁ​ምን? ለራ​ሳ​ች​ሁም አይ​ደ​ላ​ች​ሁም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ለመሆኑ፣ ሰውነታችሁ በውስጣችሁ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? ይህም መንፈስ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት ነው። እናንተም የራሳችሁ አይደላችሁም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ወይስ ሰውነታችሁ፥ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት፥ በውስጣችሁም የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆኑን አታውቁም? እናንተም የራሳችሁ አይደላችሁም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ሰውነታችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁትና በውስጣችሁም የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆኑን ታውቁ የለምን? እንግዲህ እናንተ የእግዚአብሔር ናችሁ እንጂ የራሳችሁ አይደላችሁም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19-20 ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 6:19
17 Referencias Cruzadas  

እና​ንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደስ እንደ ሆና​ችሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ስም በእ​ና​ንተ ላይ አድሮ እን​ደ​ሚ​ኖር አታ​ው​ቁ​ምን?


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦ​ትስ በጣ​ዖት ቤት ውስጥ የሚ​ያ​ኖር ማን ነው? የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪ​ያ​ዎች እኛ አይ​ደ​ለ​ን​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፥ “እኔ በእ​ነ​ርሱ አድ​ራ​ለሁ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም እኖ​ራ​ለሁ፤ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝቤ ይሆ​ኑ​ኛል።”


እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።


በዐ​ይኔ ፊት ክፉ ነገ​ርን አላ​ኖ​ር​ሁም፤ ዐመፃ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ጠላሁ።


መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


እርሱ ግን ይህን የተ​ና​ገ​ረው ቤተ መቅ​ደስ ስለ ተባለ ሰው​ነቱ ነበር።


በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ሩ​ትም ስለ እነ​ርሱ ቤዛ ሆኖ ለሞ​ተ​ውና ለተ​ነ​ሣ​ውም እንጂ ወደ​ፊት ለራ​ሳ​ቸው የሚ​ኖሩ እን​ዳ​ይ​ሆኑ እርሱ ስለ ሁሉ ቤዛ ሆኖ ሞተ።


የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​ኝም እኔ ብና​ወጥ ደስ እን​ዳ​ይ​ላ​ቸው፥


ሁሉ ከአ​ንተ ዘንድ ነውና፥ ከእ​ጅ​ህም የተ​ቀ​በ​ል​ነ​ውን ሰጥ​ተ​ን​ሃ​ልና ይህን ያህል ችለን ልና​ቀ​ር​ብ​ልህ እኔ ማን ነኝ? ሕዝ​ቤስ ማን ነው?


አክ​ዓ​ብም አዝኖ ሄደ፤ በአ​ል​ጋ​ውም ላይ ተኝቶ ፊቱን ተሸ​ፋ​ፈነ፤ እን​ጀ​ራ​ንም አል​በ​ላም።


እና​ንተ ግን ለመ​ን​ፈ​ሳዊ ሕግ እንጂ ለሥ​ጋ​ችሁ ፈቃድ የም​ት​ሠሩ አይ​ደ​ላ​ች​ሁም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በእ​ና​ንተ አድሮ ይኖ​ራ​ልና፤ የክ​ር​ስ​ቶስ መን​ፈስ ያላ​ደ​ረ​በት ግን እርሱ የእ​ርሱ ወገን አይ​ደ​ለም።


የዚ​ህ​ንስ ዓለም ዳኝ​ነት ተዉ​ትና በመ​ላ​እ​ክት ስንኳ እን​ድ​ን​ፈ​ርድ አታ​ው​ቁ​ምን?


መብል ለሆድ ነው ፤ ሆድም ለመ​ብል ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሁለ​ቱ​ንም ይሽ​ራ​ቸ​ዋል፤ ሥጋ​ች​ሁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው እንጂ ለዝ​ሙት አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሥ​ጋ​ችሁ ነው።


ወይስ መጽሐፍ “በእኛ ዘንድ ያሳደረው መንፈስ በቅንዓት ይመኛል፤” ያለው በከንቱ እንደ ተናገረ ይመስላችኋልን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios