1 ቆሮንቶስ 16:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ስመጣ ይህ የገንዘብ ማዋጣት ያንጊዜ እንዳይሆን፥ ከእናንተ ሰው ሁሉ በየሳምንቱ እሑድ የተቻለውን ያወጣጣ፤ ያገኘውንም በቤቱ ይጠብቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገንዘብ ማሰባሰብ የሚደረገው እኔ በምመጣበት ጊዜ እንዳይሆን፣ ከእናንተ እያንዳንዱ እንደ ገቢው መጠን በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን እየለየ ያስቀምጥ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ በምመጣበት ጊዜ የገንዘብ መዋጮ እንዳይደረግ፤ ከእናንተ እያንዳንዱ እንደገቢው መጠን በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን እየለየ ያስቀምጥ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ በምመጣበት ጊዜ የገንዘብ መዋጮ እንዳይደረግ በየሳምንቱ እሑድ ከእናንተ እያንዳንዱ በሚያገኘው ገቢ መጠን እያዋጣ ለይቶ ያስቀምጥ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ስመጣ ይህ የገንዘብ ማዋጣት ያን ጊዜ እንዳይሆን፥ ከእናንተ እያንዳንዱ በየሳምንቱ በፊተኛው ቀን እንደ ቀናው መጠን እያስቀረ በቤቱ ያስቀምጥ። |
ላባም፥ “በዐይንህ ፊት ሞገስን የማገኝ ብሆንስ ከዚሁ ተቀመጥ፤ እግዚአብሔር በአንተ ምክንያት እንደ ባረከኝ ተመልክቼአለሁና።
ለባሪያህ በአደረግኸው በምሕረትህና በእውነትህም ሁሉ በጎውን አድርግልኝ፤ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበርና፥ አሁን ግን የሁለት ክፍል ሠራዊት ሆንሁ።
ከወደድኸኝስ ይህችን ያመጣሁልህን በረከቴን ተቀበል፤ እግዚአብሔር ራርቶልኛልና፥ ለእኔም ብዙ አለኝና።” እስኪቀበለውም ድረስ ግድ አለው፤ ተቀበለውም።
ከሳዶቅም ወገን የሆነ ታላቁ ካህን ዓዛርያስ፥ “ሕዝቡ መባውን ወደ እግዚአብሔር ፊት ማቅረብ ከጀመረ ወዲህ በልተናል፤ ጠጥተናልም፤ ጠግበናልም፤ እግዚአብሔርም ሕዝቡን ባርኮአልና ብዙ ተርፎአል፤ ከዚህም ገና ብዙ ተረፈ” ብሎ ተናገረ።
ከሳምንቱም በመጀመሪያዪቱ ቀን ያዘጋጁትን ሽቶ ይዘው እጅግ ማልደው ወደ መቃብሩ ሄዱ፤ ሌሎች ሴቶችም አብረዋቸው ነበሩ።
ያም ከሳምንቱ የመጀመሪያው ቀን በመሸ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ አይሁድን ስለ ፈሩ ተሰብስበው የነበሩበት ቤት ደጁ ተቈልፎ ሳለ ጌታችን ኢየሱስ መጥቶ በመካከላቸው ቆመና፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው።
ከስምንት ቀን በኋላም ዳግመኛ ደቀ መዛሙርቱ በውስጡ ሳሉ፥ ቶማስም አብሮአቸው ሳለ በሩ እንደ ተዘጋ ጌታችን ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆመና፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው።
ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን እሑድ ማዕድ ለመባረክ ተሰብስበን ሳለን ጳውሎስ በማግሥቱ የሚሄድ ነውና ያስተምራቸው ጀመረ፤ እስከ መንፈቀ ሌሊትም ድረስ ትምህርቱን አስረዘመ።
በዚህም የሚጠቅማችሁን እመክራችኋለሁ፤ ይህን ከማድረጋችሁ በፊት ፈቅዳችኋልና፤ ከአምና ጀምሮም ይህን ጀምራችኋል።
ነገር ግን ዛሬ እንደ ሆነ ለአባቶችህ የማለውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ እርሱ ኀይልን ስለሚሰጥህ አምላክህን እግዚአብሔርን አስበው።