ዮሐንስ 20:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 ከስምንት ቀን በኋላም ዳግመኛ ደቀ መዛሙርቱ በውስጡ ሳሉ፥ ቶማስም አብሮአቸው ሳለ በሩ እንደ ተዘጋ ጌታችን ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆመና፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 ከስምንት ቀን በኋላም፣ ደቀ መዛሙርቱ በቤት ውስጥ ነበሩ፤ ቶማስም ከእነርሱ ጋራ ነበር፤ በሮቹ ተቈልፈው ነበር፤ ኢየሱስ ግን መጥቶ በመካከላቸው ቆመና፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” አላቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 ከስምንት ቀን በኋላም ደቀመዛሙርቱ ደግመው በቤት ውስጥ ነበሩ፤ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበረ። ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 ከስምንት ቀን በኋላ ደቀ መዛሙርቱ እንደገና በቤት ውስጥ ነበሩ፤ ቶማስም አብሮአቸው ነበር፤ በሮቹ ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጥቶ በመካከላቸው ቆመና “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” አላቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 ከስምንት ቀን በኋላም ደቀ መዛሙርቱ ደግመው በውስጥ ነበሩ፥ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበረ። ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፦ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። Ver Capítulo |