1 ዜና መዋዕል 9:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቆሬያዊውም የሰሎም በኵር ሌዋዊው ማቲትያ ለታላቁ ሊቀ ካህናት በምጣድ በሚጋገረው ነገር ላይ ሹም ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቆሬያዊው የሰሎም በኵር ልጅ ሌዋዊው ማቲትያ የቍርባኑን እንጀራ የመጋገር ኀላፊነት ተሰጥቶት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቆሬያዊውም የሰሎም በኩር ሌዋዊው ማቲትያ በምጣድ በሚጋገረው ኅብስት ላይ ሹም ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከቆሬ ጐሣ የሻሉም የበኲር ልጅ የሆነው ማቲትያ የመባውን ኅብስት የማዘጋጀት ኀላፊነት ነበረው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቆሬያዊውም የሰሎም በኵር ሌዋዊው ማቲትያ በምጣድ በሚጋገረው ነገር ላይ ሹም ነበረ። |
ደግሞም ገጸ ኅብስት፥ ስስ ቂጣም ቢሆን፥ በምጣድም ቢጋገር፥ ቢለወስም ለእህል ቍርባን በሆነው በመልካሙ ዱቄት በመስፈሪያና በልክ ሁሉ ያገለግሉ ዘንድ ሹሞአቸው ነበር።
የቆሬም ልጅ የአብያሳፍ ልጅ የቆሬ ልጅ ሰሎም ከአባቱ ቤት የነበሩ ወንድሞቹ ቆሬያውያን በማገልገል ሥራ ላይ ነበሩ፤ የድንኳኑንም መድረክ ይጠብቁ ነበር። አባቶቻቸውም የእግዚአብሔርን ሰፈር መግቢያ ይጠብቁ ነበር።
የመድረኩ በረኞች ይሆኑ ዘንድ የተመረጡ እነዚህ ሁሉ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ነበሩ። እነዚህ በመንደሮቻቸው በየትውልዳቸው ተቈጠሩ። ዳዊትና ነቢዩ ሳሙኤል ታማኝነታቸውን አይተው በሥራቸው አቆሙአቸው።
እነዚህ አራቱ ኀያላን ሰዎች ለአራቱ በሮች ኀላፊዎች ነበሩ። ሌዋውያንም በእግዚአብሔር ቤት ባሉ ጓዳዎችና ቤተ መዛግብት ላይ የተሾሙ ነበሩ።
ከዘይት ጋር በምጣድ ላይ ያደርጉታል፤ ለውሰውም ያገቡታል፤ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን የሚፈተት መሥዋዕት ነው።