Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 9:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 የመ​ድ​ረኩ በረ​ኞች ይሆኑ ዘንድ የተ​መ​ረጡ እነ​ዚህ ሁሉ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ነበሩ። እነ​ዚህ በመ​ን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው ተቈ​ጠሩ። ዳዊ​ትና ነቢዩ ሳሙ​ኤል ታማ​ኝ​ነ​ታ​ቸ​ውን አይ​ተው በሥ​ራ​ቸው አቆ​ሙ​አ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 መግቢያ በሮቹን በኀላፊነት እንዲጠብቁ የተመረጡት በአጠቃላይ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ነበሩ። እነርሱም በትውልድ ሐረጋቸው መሠረት በሚኖሩባቸው መንደሮች ተቈጥረው ተመዘገቡ፤ በር ጠባቂዎቹን በዚያ ቦታ ላይ የመደቧቸው ዳዊትና ባለራእዩ ሳሙኤል ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 የመግቢያው ደጅ ጠባቂዎች እንዲሆኑ የተመረጡ እነዚህ ሁሉ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ዳዊትና ነቢዩ ሳሙኤል በሥራቸው ያቆሙአቸው እነዚህ በመንደሮቻቸው በየትውልዳቸው ተቈጠሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 መግቢያ በሮችንና ቅጽር በሮችን ለመጠበቅ የተመረጡ በአጠቃላይ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱም በሚኖሩባቸው መንደሮች መሠረት ተቈጥረው ተመዘገቡ፤ የእነርሱን የቀድሞ አባቶች በዚህ ኀላፊነት የመደቡአቸው ንጉሥ ዳዊትና ነቢዩ ሳሙኤል ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 የመድረኩ በረኞች ይሆኑ ዘንድ የተመረጡ እነዚህ ሁሉ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ዳዊትና ነቢዩ ሳሙኤል በሥራቸው ያቆሙአቸው እነዚህ በመንደሮቻቸው በየትውልዳቸው ተቈጠሩ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 9:22
18 Referencias Cruzadas  

የካ​ህ​ና​ቱ​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑ​ንም ክፍ​ላ​ቸ​ውን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በት ሥራ ሁሉ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በት ዕቃ ሁሉ፥ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ ለሚ​ሆ​ነ​ውም፥


እነ​ሆም፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ የሚ​ሆኑ የካ​ህ​ና​ትና የሌ​ዋ​ው​ያን ክፍ​ሎች በዚህ አሉ፤ ለሁ​ሉም ዓይ​ነት አገ​ል​ግ​ሎ​ትና ሥራ በጥ​በ​ብና በነ​ፍሱ ፈቃድ የሚ​ሠራ ሁሉ ከአ​ንተ ጋር ይሆ​ናል፤ አለ​ቆ​ችና ሕዝ​ቡም ሁሉ ፈጽ​መው ይታ​ዘ​ዙ​ሃል” አለው።


የን​ጉ​ሡም የዳ​ዊት የፊ​ተ​ኛ​ውና የኋ​ለ​ኛው ነገር፥ እነሆ፥ በባ​ለ​ራ​እዩ በሳ​ሙ​ኤል ታሪክ፥ በነ​ቢ​ዩም በና​ታን ታሪክ፥ በባለ ራእ​ዩም በጋድ ታሪክ ተጽ​ፎ​አል።


በነ​ጦ​ፋ​ው​ያ​ንም መን​ደ​ሮች የተ​ቀ​መ​ጠው የሕ​ል​ቃና ልጅ የአሳ ልጅ በራ​ክያ።


እነ​ር​ሱና ልጆ​ቻ​ቸ​ውም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በድ​ን​ኳኑ ደጆች ላይ በረ​ኞች ነበሩ።


የቆ​ሬ​ያ​ዊ​ውም የሰ​ሎም በኵር ሌዋ​ዊው ማቲ​ትያ ለታ​ላቁ ሊቀ ካህ​ናት በም​ጣድ በሚ​ጋ​ገ​ረው ነገር ላይ ሹም ነበረ።


በማ​ና​ቸ​ውም ነገር ሁሉ ርኩስ የሆነ ሰው እን​ዳ​ይ​ገባ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በር በረ​ኞ​ችን አኖረ።


በካ​ህ​ና​ቱም ከተ​ሞች ለታ​ላ​ላ​ቆ​ችና ለታ​ና​ና​ሾች ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ክፍ​ላ​ቸ​ውን በእ​ም​ነት ይሰጡ ዘንድ ኤዶም፥ ብን​ያስ፥ ኢያሱ፥ ሴሚ፥ አማ​ርያ፥ ኮክ​ን​ያስ ከእጁ በታች ነበሩ።


በማ​ኅ​በ​ራ​ቸ​ውም ሁሉ በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው ለተ​ቈ​ጠሩ ለሚ​ስ​ቶ​ቻ​ቸው፥ ለወ​ን​ዶ​ችና ለሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ይሰጡ ነበር፤ በእ​ም​ነት ፈጽ​መው ተቀ​ድ​ሰ​ዋ​ልና።


ከሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ተከ​ፍ​ለው በይ​ሁ​ዳና በብ​ን​ያም ነበሩ።


የይ​ሁ​ዳም ሕዝብ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን ደስ ስላ​ላ​ቸው፥ የካ​ህ​ና​ቱ​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑን ዕድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከ​ተ​ሞች እር​ሻ​ዎች ያከ​ማቹ ዘንድ ለቀ​ዳ​ም​ያት፥ ለዐ​ሥ​ራ​ትም በየ​ዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎ​ችን ሾሙ።


ቀድሞ ነቢ​ዩን ባለ ራእይ ይሉት ነበ​ርና አስ​ቀ​ድሞ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመ​ጠ​የቅ ሲሄድ፦ ኑ፤ ወደ ባለ ራእይ እን​ሂድ ይል ነበር።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos