Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 6:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 “የአ​ሮን ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመ​ሠ​ዊ​ያው ፊት ለፊት የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የመ​ሥ​ዋ​ዕት ሥር​ዐት ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “ ‘የእህል ቍርባን ሥርዐት ይህ ነው፦ የአሮን ልጆች ቍርባኑን በመሠዊያው ትይዩ በእግዚአብሔር ፊት ያቅርቡት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 “የእህሉም ቁርባን ሕግ ይህ ነው፤ የአሮን ልጆች በመሠዊያው ፊት ለፊት በጌታ ፊት ያቀርቡታል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 “ስለ እህል መባ አቀራረብ የተደነገጉት መመሪያዎች እነዚህ ናቸው፦ ትውልዱ ከአሮን ዘር የሆነ ካህን የእህሉን መባ በመሠዊያው ፊት ለፊት ለእግዚአብሔር ያቅርብ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የእህሉም ቍርባን ሕግ ይህ ነው፤ የአሮን ልጆች በእግዚአብሔር ፊት በመሠዊያው ፊት ያቀርቡታል።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 6:14
12 Referencias Cruzadas  

የቆ​ሬ​ያ​ዊ​ውም የሰ​ሎም በኵር ሌዋ​ዊው ማቲ​ትያ ለታ​ላቁ ሊቀ ካህ​ናት በም​ጣድ በሚ​ጋ​ገ​ረው ነገር ላይ ሹም ነበረ።


የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹን ግን በውኃ ያጥ​ቡ​ታል። ካህ​ኑም ሁሉን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ለቍ​ር​ባን ያቀ​ር​በ​ዋል፤ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጎ መዓዛ ያለው ቍር​ባን ነው።


ከክ​ን​ፎ​ቹም ይሰ​ብ​ረ​ዋል፤ ነገር ግን አይ​ለ​የ​ውም። ካህ​ኑም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በእ​ሳቱ ላይ ባለው በዕ​ን​ጨቱ ላይ ያኖ​ረ​ዋል፤ መሥ​ዋ​ዕቱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው ቍር​ባን ነው።


የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹን ግን በውኃ ያጥ​ባሉ፤ ካህ​ኑም ሁሉን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል።


ሙሴም አሮ​ንን፥ የተ​ረ​ፉ​ለ​ትን ልጆ​ቹን አል​ዓ​ዛ​ር​ንና ኢታ​ም​ርን አላ​ቸው፥ “ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነውና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆ​ነው ከእ​ሳት ቍር​ባን የቀ​ረ​ውን የስ​ን​ዴ​ውን ቍር​ባን ውሰዱ፤ ቂጣም አድ​ር​ጋ​ችሁ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ ብሉት፤


ዘወ​ትር በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ እሳት ይነ​ድ​ዳል፤ አይ​ጠ​ፋም።


ካህ​ኑም ከእ​ህሉ ቍር​ባን መል​ካ​ሙን የስ​ንዴ ዱቄት ከዘ​ይት ጋር እፍኝ ሙሉ፥ ደግ​ሞም በእ​ህሉ ቍር​ባን ላይ ያለ​ውን ዕጣን ሁሉ ያነ​ሣል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ መዓዛ ያለው የመ​ታ​ሰ​ቢያ ቍር​ባን እን​ዲ​ሆን ለመ​ታ​ሰ​ቢያ ነውና በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል።


ቍር​ባ​ኑን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ርብ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ በሆነ ዘይት የተ​ለ​ወሰ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ እጅ የሆነ የመ​ል​ካም ዱቄት መሥ​ዋ​ዕት ያመ​ጣል።


ለአ​ን​ዱም አውራ በግ የሚ​ቃ​ጠል ቍር​ባን ወይም መሥ​ዋ​ዕት ባደ​ረ​ጋ​ችሁ ጊዜ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ሢሶ በሆነ ዘይት የተ​ለ​ወሰ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ መል​ካም ዱቄት ለእ​ህል ቍር​ባን ታዘ​ጋ​ጃ​ላ​ችሁ።


በላሙ ላይ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ግማሽ በሆነ ዘይት የተ​ለ​ወሰ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ መል​ካም ዱቄት ለእ​ህል ቍር​ባን ታቀ​ር​ባ​ለህ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ያን እን​ጀራ ከሰ​ማይ የሰ​ጣ​ችሁ ሙሴ አይ​ደ​ለም፤ አባቴ ከሰ​ማይ የእ​ው​ነት እን​ጀ​ራን ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋል እንጂ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos