1 ዜና መዋዕል 26:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ ሰሎሚትና ወንድሞቹ፥ ንጉሡ ዳዊትና የአባቶች ቤቶች አለቆች፥ ሻለቆችና የመቶ አለቆች፥ የሠራዊቱም አለቆች፥ በቀደሱት በንዋየ ቅድሳቱ ቤተ መዛግብት ሁሉ ላይ ተሹመው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰሎሚትና የሥጋ ዘመዶቹ ንጉሥ ዳዊት፣ የቤተ ሰቡ ኀላፊዎች፣ የሻለቆችና የመቶ አለቆች እንዲሁም ሌሎች የሰራዊቱ አዛዦች ቀድሰው ላቀረቧቸው ንዋያተ ቅድሳት ኀላፊዎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ሰሎሚትና ወንድሞቹ ንጉሡ ዳዊትና የአባቶች ቤቶች አለቆች፥ ሻለቆችና የመቶ አለቆች የሠራዊቱም አዛዦች፥ በቀደሱት በንዋየ ቅድሳቱ ቤተ መዛግብት ሁሉ ላይ ተሾመው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሸሎሚትና ዘመዶቹ ንጉሥ ዳዊት የቤተሰብ አለቆች፥ የጐሣ ቡድን መሪዎችና የጦር መኰንኖች ለእግዚአብሔር የተለዩ አድርገው ላቀረቡአቸው ስጦታዎች ኀላፊዎች ነበሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ ሰሎሚትና ወንድሞቹ ንጉሡ ዳዊትና የአባቶች ቤቶች አለቆች፥ ሻለቆችና የመቶ አለቆች የሠራዊቱም አለቆች፥ በቀደሱት በንዋየ ቅድሳቱ ቤተ መዛግብት ሁሉ ላይ ተሾመው ነበር። |
ንጉሡም ዳዊት ከአሕዛብ ሁሉ ከኤዶምና ከሞዓብ፥ ከአሞንም ልጆች፥ ከፍልስጥኤማውያንም፥ ከአማሌቅም ከማረከው ብርና ወርቅ ጋር እነዚህን ደግሞ ለእግዚአብሔር ቀደሰ።
አሁንም፥ እነሆ፥ በድህነቴ ለእግዚአብሔር ቤት መቶ ሺህ መክሊት ወርቅና አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፥ ሚዛንም የሌላቸው ብዙ ናስና ብረት አዘጋጅቻለሁ፤ ደግሞም የማይቈጠር ብዙ የዝግባ እንጨትና ድንጋዮች አዘጋጅቻለሁ፤ አንተም ልጄ ከዚያ በላይ ጨምር።
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሕንጻ ወደ ኋላ እንዳይል ዳዊት ከየሀገሩ በማረካቸውና በሰበሰባቸው በቀደሳቸውም ላይ የተሾሙ ናቸው።
እነሆም፥ ለእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ሁሉ የሚሆኑ የካህናትና የሌዋውያን ክፍሎች በዚህ አሉ፤ ለሁሉም ዓይነት አገልግሎትና ሥራ በጥበብና በነፍሱ ፈቃድ የሚሠራ ሁሉ ከአንተ ጋር ይሆናል፤ አለቆችና ሕዝቡም ሁሉ ፈጽመው ይታዘዙሃል” አለው።
ሌዋውያንና ይሁዳም ሁሉ ካህኑ ኢዮአዳ ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ፤ ካህኑም ኢዮአዳ ሰሞነኞቹን አላሰናበተም ነበርና እያንዳንዱ ከሰንበት መጀመሪያ እስከ ሰንበት መጨረሻ ሰዎችን ወሰደ።
ሕዝቅያስም የካህናትንና የሌዋውያንን ሰሞን በየክፍላቸውና በየአገልግሎታቸው፥ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ በሮች የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቀርቡና ያገለግሉ ዘንድ፥ ያመሰግኑም፥ ያከብሩም ዘንድ ካህናቱንና ሌዋውያኑን መደበ።
የበረኞች ልጆች፥ የሰሎም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጤልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሰበዋይ ልጆች ሁሉ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ።
እነርሱም መዘምራኑና በረኞቹም የአምላካቸውን ሥርዐት የመንጻታቸውን ሥርዐት እንደ ዳዊትና እንደ ልጁ እንደ ሰሎሞን ትእዛዝ ጠበቁ።