Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 28:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እነ​ሆም፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ የሚ​ሆኑ የካ​ህ​ና​ትና የሌ​ዋ​ው​ያን ክፍ​ሎች በዚህ አሉ፤ ለሁ​ሉም ዓይ​ነት አገ​ል​ግ​ሎ​ትና ሥራ በጥ​በ​ብና በነ​ፍሱ ፈቃድ የሚ​ሠራ ሁሉ ከአ​ንተ ጋር ይሆ​ናል፤ አለ​ቆ​ችና ሕዝ​ቡም ሁሉ ፈጽ​መው ይታ​ዘ​ዙ​ሃል” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ ሁሉ የሚያስፈልጉት ካህናትና ሌዋውያን ምድብም ዝግጁ ነው። በሁሉም የእጅ ሙያ የሠለጠኑ ፈቃደኛ ሰዎች በሥራው ሁሉ ይረዱሃል። ሹማምቱና ሕዝቡ ሁሉ ትእዛዝህን ይፈጽማሉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እነሆም፥ ለእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ሁሉ የሚሆኑ የካህናትና የሌዋውያን ክፍሎች በዚህ አሉ፤ ለሁሉም ዓይነት አገልግሎትና ሥራ በብልሃትና በነፍሱ ፈቃድ የሚሠራ ሁሉ ከአንተ ጋር ይሆናል፤ አለቆችና ሕዝቡም ሁሉ ፈጽመው ይታዘዙሃል።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያለውን አገልግሎት እንዲፈጽሙ ካህናትና ሌዋውያን ተመድበዋል፤ ልዩ ልዩ ችሎታ ያላቸው ሠራተኞች ይረዱሃል፤ ሕዝቡና መሪዎቻቸው ሁሉ ለአንተ ይታዘዛሉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እነሆም፥ ለእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ሁሉ የሚሆኑ የካህናትና የሌዋውያን ክፍሎች በዚህ አሉ፤ ለሁሉም ዐይነት አገልግሎትና ሥራ በብልሃትና በነፍሱ ፈቃድ የሚሠራ ሁሉ ከአንተ ጋር ይሆናል፤ አለቆችና ሕዝቡም ሁሉ ፈጽመው ይታዘዙሃል፤” አለው።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 28:21
12 Referencias Cruzadas  

ዐሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ለሐ​ናኒ ለል​ጆ​ቹም፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ፤


ይህ ሰሎ​ሚ​ትና ወን​ድ​ሞቹ፥ ንጉሡ ዳዊ​ትና የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች፥ ሻለ​ቆ​ችና የመቶ አለ​ቆች፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለ​ቆች፥ በቀ​ደ​ሱት በን​ዋየ ቅድ​ሳቱ ቤተ መዛ​ግ​ብት ሁሉ ላይ ተሹ​መው ነበር።


የካ​ህ​ና​ቱ​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑ​ንም ክፍ​ላ​ቸ​ውን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በት ሥራ ሁሉ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በት ዕቃ ሁሉ፥ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ ለሚ​ሆ​ነ​ውም፥


ሥራው ምስ​ጋ​ናና የጌ​ት​ነት ክብር ነው። ጽድ​ቁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።


በሥራ ሁሉ ያስ​ተ​ውል ዘንድ በጥ​በ​ብም፥ በማ​ስ​ተ​ዋ​ልም፥ በዕ​ው​ቀ​ትም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ፈስ ሞላ​ሁ​በት፤


በል​ባ​ቸው ጥበ​በ​ኞች የሆኑ ሴቶ​ችም በእ​ጃ​ቸው ፈተሉ፤ የፈ​ተ​ሉ​ት​ንም ሰማ​ያ​ዊ​ውን፥ ሐም​ራ​ዊ​ው​ንም፥ ቀዩ​ንም ግምጃ፥ ጥሩ​ው​ንም በፍታ አመጡ።


“ባስ​ል​ኤ​ልና ኤል​ያብ፥ ለመ​ቅ​ደ​ስም ማገ​ል​ገያ ሥራ ሁሉ ያደ​ርጉ ዘንድ እን​ዲ​ያ​ውቁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን የሰ​ጣ​ቸው በል​ባ​ቸ​ውም ጥበ​በ​ኞች የሆኑ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ነገር ሁሉ አደ​ረጉ።”


ሙሴም ባስ​ል​ኤ​ል​ንና ኤል​ያ​ብን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዕው​ቀ​ት​ንና ጥበ​ብን በል​ቡ​ና​ቸው ያሳ​ደ​ረ​ባ​ቸ​ው​ንና ጥበብ ያላ​ቸ​ውን፥ ሥራ​ው​ንም ለመ​ሥ​ራት ይቀ​ርብ ዘንድ ልቡ ያስ​ነ​ሣ​ውን ሁሉ ሥራ​ውን ሠር​ተው ይፈ​ጽሙ ዘንድ ጠራ​ቸው።


ሰው ሁሉ በበ​ላይ ላሉ ባለ​ሥ​ል​ጣ​ኖች ይገዛ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ል​ተ​ገኘ በቀር ሥል​ጣን የለ​ምና፤ ያሉ​ትም ባለ​ሥ​ል​ጣ​ኖች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሾሙ ናቸው።


ለገዦችና ለባለ ሥልጣኖች የሚገዙና የሚታዘዙ፥ ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጁ፥ ማንንም የማይሰድቡ፥ የማይከራከሩ፥ ገሮች፥ ለሰው ሁሉ የዋህነትን ሁሉ የሚያሳዩ እንዲሆኑ ኣሳስባቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos