አብርሃምም ማልዶ ተነሣ፤ እንጀራንም ወሰደ፤ የውኃ አቍማዳንም ለአጋር በትከሻዋ አሸከማት፤ ሕፃኑንም ሰጥቶ አስወጣት፤ እርስዋም ሄደች፤ በዐዘቅተ መሐላም በኩል ባለው ምድረ በዳ ተቅበዘበዘች።
1 ዜና መዋዕል 21:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ኢዮአብንና የሕዝቡን አለቆች ሁሉ፥ “ሂዱ፥ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ዳን ድረስ እስራኤልን ቍጠሩ፤ ድምራቸውንም አውቅ ዘንድ አስታውቁኝ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም ኢዮአብንና የሰራዊቱን አዛዦች፣ “ሄዳችሁ ከቤርሳቤህ እስከ ዳን ያሉትን እስራኤላውያን ቍጠሩ፤ ከዚያም ምን ያህል እንደ ሆኑ ዐውቅ ዘንድ ንገሩኝ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም ኢዮአብንና የሕዝቡን አለቆች፦ “ሂዱ፥ ከቤር-ሳቤህ ጀምሮ እስከ ዳን ድረስ እስራኤልን ቁጠሩ፥ ድምራቸውንም እንዳውቅ ተመልሳችሁ አስታውቁኝ” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት ለኢዮአብና ለሌሎቹ የጦር መኰንኖች “በመላው እስራኤል ከአገሪቱ ዳር እስከ ዳር፥ ማለትም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ሄዳችሁ ሕዝቡን ቊጠሩ፤ እኔ በእስራኤል ምን ያኽል ሕዝብ እንዳለ ማወቅ እፈልጋለሁ” የሚል ትእዛዝ ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ኢዮአብንና የሕዝቡን አለቆች “ሂዱ፤ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ዳን ድረስ እስራኤልን ቍጠሩ፤ ድምራቸውንም አውቅ ዘንድ አስታውቁኝ፤” አላቸው። |
አብርሃምም ማልዶ ተነሣ፤ እንጀራንም ወሰደ፤ የውኃ አቍማዳንም ለአጋር በትከሻዋ አሸከማት፤ ሕፃኑንም ሰጥቶ አስወጣት፤ እርስዋም ሄደች፤ በዐዘቅተ መሐላም በኩል ባለው ምድረ በዳ ተቅበዘበዘች።
እኔ እንዲህ እመክርሃለሁ፤ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እስራኤል ሁሉ ብዛታቸው እንደ ባሕር አሸዋ ሆኖ ወደ አንተ ይሰብሰቡ፤ አንተም በመካከላቸው ትሄዳለህ።
ዳዊትም ቸነፈሩን መረጠ፤ የስንዴም መከር ወራት በሆነ ጊዜ ጌታ ከጥዋት እስከ ቀትር ቸነፈርን በእስራኤል ላይ ላከ። ቸነፈሩም በሕዝቡ መካከል ጀመረ፤ ከሕዝቡም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ሰባ ሺህ ሰው ሞተ።
የዳዊትንም ዙፋን በእስራኤልና በይሁዳ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ከፍ ያደርግ ዘንድ መንግሥትን ከሳኦል ቤት ወሰዳት።”
በሰሎሞንም ዘመን ሁሉ ይሁዳና እስራኤል ከዳን ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ እያንዳንዳቸው ከወይኑና ከበለሱ በታች ተዘልለው ይቀመጡ ነበር።
እንደ ተጻፈም ብዙዎቹ አላደረጉትም ነበርና የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ፋሲካ በኢየሩሳሌም ያደርጉ ዘንድ እንዲመጡ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ዳን ድረስ ለእስራኤል ሁሉ አዋጅ እንዲነገር ወሰኑ።
የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ወጡ፤ ማኅበሩም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ፥ ከገለዓድም ሰዎች ጋር፥ ወደ እግዚአብሔር ወደ መሴፋ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ።