Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 21:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ኢዮ​አ​ብም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝቡ ላይ አሁን ባለ​በት መቶ እጥፍ ይጨ​ምር፤ የጌ​ታዬ የን​ጉሥ ዐይ​ኖ​ችም ይዩ፤ ሁሉም የጌ​ታዬ አገ​ል​ጋ​ዮች ናቸው፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በደል ይሆን ዘንድ ይህን ነገር ጌታዬ ለምን ይሻል?” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ኢዮአብ ግን፣ “እግዚአብሔር የእስራኤልን ሰራዊት አሁን ካለው በላይ በመቶ ዕጥፍ ያብዛው፤ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ ሁሉስ ቢሆኑ የጌታዬ ተገዦች አይደሉምን? ታዲያ ንጉሡ ጌታዬ ይህን ማድረግ ለምን አስፈለገው? ለምንስ በእስራኤል ላይ በደል ያመጣል?” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ኢዮአብም አለ፦ “ጌታ ሕዝቡን በአሁኑ ላይ መቶ እጥፍ ይጨምር፤ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! ሁሉ የጌታዬ ባርያዎች አይደሉምን? ይህን ነገር ጌታዬ ለምን ይሻል? በእስራኤል ላይ በደል ስለምን ያመጣል?”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ኢዮአብም “ንጉሥ ሆይ፥ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ አሁን ካሉት ይልቅ በመቶ እጅ ያብዛልህ! እነርሱ በሙሉ የአንተ አገልጋዮች ናቸው፤ ታዲያ አንተ የሕዝብ ቈጠራ በማድረግ ሕዝቡን በሙሉ በደለኛ ለምን ታደርጋለህ?” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ኢዮአብም “እግዚአብሔር ሕዝቡን በአሁኑ ላይ መቶ እጥፍ ይጨምር፤ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! ሁሉ የጌታዬ ባሪያዎች አይደሉምን? ይህን ነገር ጌታዬ ለምን ይሻል? በእስራኤል ላይ በደል ስለ ምን ያመጣል?” አለ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 21:3
15 Referencias Cruzadas  

የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ቍጥር ላይ እልፍ አእ​ላ​ፋት ይጨ​ምር፤ እንደ ተና​ገ​ራ​ች​ሁም ይባ​ር​ካ​ችሁ።


ዘር​ህም እንደ አሸዋ የሆ​ድ​ህም ትው​ልድ እንደ ምድር ትቢያ በሆነ ነበር፤ አሁ​ንም ስምህ ከፊቴ ባል​ጠ​ፋና ባል​ፈ​ረሰ ነበር።


አቤቱ፥ ክፋ​ትን ጨም​ር​ባ​ቸው፤ ለም​ድር ክቡ​ራን ክፋ​ትን ጨም​ር​ባ​ቸው።


የንጉሥ ክብር በሕዝብ ብዛት ነው፤ የገዥ ውድቀት ግን በሕዝብ ማነስ ነው።


አይ​ዞህ፥ በርታ፤ ስለ ሕዝ​ባ​ች​ንና ስለ አም​ላ​ካ​ች​ንም ከተ​ሞች እን​በ​ርታ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፊቱ ደስ ያሰ​ኘ​ውን ያድ​ርግ” አለ።


ስለ በደ​ለ​ውና እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ስላ​ሳ​ተ​በት ስለ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት እስ​ራ​ኤ​ልን ይጥ​ላል።”


ልጆቼ ሆይ፥ ይህ አይ​ሆ​ንም፤ እኔ የም​ሰ​ማው ይህ ነገር መል​ካም አይ​ደ​ለ​ምና እን​ዲህ አታ​ድ​ርጉ። ሕዝ​ቡ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከማ​ገ​ል​ገል አት​ከ​ል​ክ​ሉ​አ​ቸው።


ሙሴም አሮ​ንን፥ “ይህን ታላቅ ኀጢ​አት ታመ​ጣ​በት ዘንድ ይህ ሕዝብ ምን አደ​ረ​ገህ?” አለው።


አቤ​ሜ​ሌ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን ጠርቶ አለው፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ምን​ድን ነው? ምንስ ክፉ ሠራ​ሁ​ብህ? በእ​ኔና በመ​ን​ግ​ሥቴ ላይ ትልቅ ኀጢ​አት አው​ር​ደ​ሃ​ልና፤ ማንም የማ​ያ​ደ​ር​ገው የማ​ይ​ገባ ሥራ በእኔ ሠራ​ህ​ብኝ።”


ነገር ግን የን​ጉሡ ቃል በኢ​ዮ​አብ ላይ አሸ​ነፈ፤ ኢዮ​አ​ብም ወጥቶ በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ ተዘ​ዋ​ወረ፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም መጣ።


“አንተ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ቍጥር የወ​ሰ​ድህ እንደ ሆነ በቈ​ጠ​ር​ሃ​ቸው ጊዜ መቅ​ሠ​ፍት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው፥ በቈ​ጠ​ር​ሃ​ቸው ጊዜ ከእ​ነ​ርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቍጥ​ራ​ቸው መጠን የነ​ፍ​ሱን ቤዛ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይስጥ።


በገ​ለ​ዓ​ድም ምድር ወዳ​ሉት ወደ ሮቤል ልጆ​ችና ወደ ጋድ ልጆች፥ ወደ ምና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ደረሱ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ነገ​ሩ​አ​ቸው


ኢዮ​አ​ስም ካህ​ኑን ዮዳ​ሄ​ንና ካህ​ና​ቱን ጠርቶ፥ “በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ የተ​ና​ዱ​ትን ስፍ​ራ​ዎች ስለ ምን አል​ጠ​ገ​ና​ች​ሁም? ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ ገን​ዘቡ ለቤቱ መጠ​ገኛ ይሰጥ እንጂ ከሚ​ያ​መ​ጡት ሰዎች አት​ቀ​በሉ” አላ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios