እንዲህም ሆነ፤ በዓመቱ መጨረሻ ነገሥታት ወደ ሰልፍ በሚወጡበት ጊዜ፥ ዳዊት ኢዮአብን ከእርሱም ጋር አገልጋዮቹን፥ እስራኤልንም ሁሉ ሰደደ። የአሞንንም ልጆች አጠፉ፤ አራቦትንም ከበቡ፤ ዳዊት ግን በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር።
1 ዜና መዋዕል 20:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ በዓመት መጨረሻ ነገሥታት ወደ ሰልፍ በሚወጡበት ጊዜ ኢዮአብ የሠራዊቱን ኀይል አወጣ፤ የአሞንንም ልጆች ሀገር አጠፋ፤ መጥቶም አራቦትን ከበበ። ዳዊትም በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ነበር። ኢዮአብም አራቦትን መትቶ አፈረሳት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገሥታት ለጦርነት በሚወጡበት በጸደይ ወራት፣ ኢዮአብ የጦር ሰራዊቱን እየመራ ሄዶ የአሞናውያንን አገር አጠፋ፤ ወደ ረባትም ሄዶ ከበባት፤ ዳዊት ግን በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር። ኢዮአብም ረባትን ወግቶ አፈራረሳት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ሆነ፤ በዓመት መለወጫ ነገሥታት ወደ ጦርነት በሚወጡበት ጊዜ ኢዮአብ ሠራዊቱን አወጣ፥ የአሞንንም ልጆች አገር አጠፋ፤ መጥቶም ረባትን ከበበ። ዳዊትም በኢየሩሳሌም ቈይቶ ነበር። ኢዮአብም ረባትን መትቶ አፈረሳት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተከታዩ የዓመት መባቻ ማለትም ነገሥታት አብዛኛውን ጊዜ ወደ ጦርነት በሚሄዱበት ወራት፥ ኢዮአብ ሠራዊቱን እየመራ ሄዶ የዐሞንን አገር ወረረ፤ ንጉሥ ዳዊት ግን በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፤ የኢዮአብ ሠራዊትም የራባን ከተማ ከበው አደጋ በመጣል ደመሰሱአት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፤ በዓመት መለወጫ ነገሥታት ወደ ሰልፍ በሚወጡበት ጊዜ ኢዮአብ ሠራዊቱን አወጣ፤ የአሞንንም ልጆች አገር አጠፋ፤ መጥቶም ረባትን ከበበ። ዳዊትም በኢየሩሳሌም ቈይቶ ነበር። ኢዮአብም ረባትን መትቶ አፈረሳት። |
እንዲህም ሆነ፤ በዓመቱ መጨረሻ ነገሥታት ወደ ሰልፍ በሚወጡበት ጊዜ፥ ዳዊት ኢዮአብን ከእርሱም ጋር አገልጋዮቹን፥ እስራኤልንም ሁሉ ሰደደ። የአሞንንም ልጆች አጠፉ፤ አራቦትንም ከበቡ፤ ዳዊት ግን በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር።
ዳዊትም ወደ ምናሄም በመጣ ጊዜ በአሞን ልጆች ሀገር በአራቦት የነበረ የነዓሶን ልጅ ኡኤሴብ፥ የሎዶባርም ሰው የአሜሄል ልጅ ማኪር፥ የሮጌሌምም ሰው ገለዓዳዊው ቤርዜሊ፥
በሥራህም አስቈጥተኸኛልና፥ እስራኤልንም አስተሃልና ቤትህን እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮርብዓም ቤት እንደ አኪያም ልጅ እንደ ባኦስ ቤት አደርገዋለሁ።”
እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት ያጠፋቸው አሞራውያን እንደ ሠሩት ሁሉ፥ ጣዖትን በመከተል እጅግ ርኩስ ነገርን ሠራ።
የአድርአዛርም አገልጋዮች በእስራኤል ፊት እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ ከዳዊት ጋር ታረቁ፤ ተገዙለትም፤ ሶርያውያንም ከዚያ ወዲያ የአሞንን ልጆች ይረዱ ዘንድ እንቢ አሉ።
እነሆ፥ ፍሙን በወናፍ እንደሚያናፋ፥ ለሥራውም መሣሪያ እንደሚያወጣ ብረት ሠሪ የፈጠርሁሽ አይደለም፤ እኔ ግን ለመልካም ፈጠርሁሽ እንጂ ለጥፋት አይደለም።
እኔም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?” አልሁ። እርሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፥ “ከተሞች የሚኖርባቸውን አጥተው እስኪፈርሱ ድረስ፥ ቤቶችም ሰው አልቦ እስኪሆኑ፥ ምድርም ፈጽሞ ባድማ ሆና እስክትቀር ድረስ ነው፤”
የአሞንን ከተማ ለግመሎች ማሰማሪያ፥ የአሞንንም ልጆች ለመንጋ መመሰጊያ አደርጋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
በራባ ቅጥር ላይ እሳትን አነድዳለሁ፤ በጦርነት ቀን በጩኸት መሠረቶችዋን ትበላለች፤ በፍጻሜዋም ቀን ትናወጣለች።
ከራፋይንም ወገን የባሳን ንጉሥ ዐግ ብቻውን ቀርቶ ነበር፤ እነሆ፥ አልጋው የብረት አልጋ ነበረ፤ እርሱ በአሞን ልጆች ሀገር ዳርቻ አለ፤ ርዝመቱ ዘጠኝ ክንድ ወርዱም አራት ክንድ በሰው ክንድ ልክ ነበረ።