1 ዜና መዋዕል 20:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 እንዲህም ሆነ፤ በዓመት መለወጫ ነገሥታት ወደ ጦርነት በሚወጡበት ጊዜ ኢዮአብ ሠራዊቱን አወጣ፥ የአሞንንም ልጆች አገር አጠፋ፤ መጥቶም ረባትን ከበበ። ዳዊትም በኢየሩሳሌም ቈይቶ ነበር። ኢዮአብም ረባትን መትቶ አፈረሳት። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ነገሥታት ለጦርነት በሚወጡበት በጸደይ ወራት፣ ኢዮአብ የጦር ሰራዊቱን እየመራ ሄዶ የአሞናውያንን አገር አጠፋ፤ ወደ ረባትም ሄዶ ከበባት፤ ዳዊት ግን በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር። ኢዮአብም ረባትን ወግቶ አፈራረሳት። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 በተከታዩ የዓመት መባቻ ማለትም ነገሥታት አብዛኛውን ጊዜ ወደ ጦርነት በሚሄዱበት ወራት፥ ኢዮአብ ሠራዊቱን እየመራ ሄዶ የዐሞንን አገር ወረረ፤ ንጉሥ ዳዊት ግን በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፤ የኢዮአብ ሠራዊትም የራባን ከተማ ከበው አደጋ በመጣል ደመሰሱአት፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 እንዲህም ሆነ፤ በዓመት መጨረሻ ነገሥታት ወደ ሰልፍ በሚወጡበት ጊዜ ኢዮአብ የሠራዊቱን ኀይል አወጣ፤ የአሞንንም ልጆች ሀገር አጠፋ፤ መጥቶም አራቦትን ከበበ። ዳዊትም በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ነበር። ኢዮአብም አራቦትን መትቶ አፈረሳት። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 እንዲህም ሆነ፤ በዓመት መለወጫ ነገሥታት ወደ ሰልፍ በሚወጡበት ጊዜ ኢዮአብ ሠራዊቱን አወጣ፤ የአሞንንም ልጆች አገር አጠፋ፤ መጥቶም ረባትን ከበበ። ዳዊትም በኢየሩሳሌም ቈይቶ ነበር። ኢዮአብም ረባትን መትቶ አፈረሳት። Ver Capítulo |