ከዚያም በሄደ ጊዜ የሬካብን ልጅ ኢዮናዳብን በመንገድ አገኘው፤ ተቀብሎም መረቀው፤ ኢዩም፥ “ልቤ ከልብህ ጋር ቅን እንደ ሆነ ያህል ልብህ ከልቤ ጋር በቅንነት ነውን?” አለው። ኢዮናዳብም፥ “አዎን” አለው። ኢዩም፥ “እውነትህስ ከሆነ እጅህን ስጠኝ” አለ። እጁንም ሰጠው፤ ወደ እርሱም ወደ ሰረገላው አወጣው።
1 ዜና መዋዕል 2:55 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በያቤጽም የተቀመጡ የጸሓፊዎች ወገኖች፤ ቴርዓውያን፥ ሹማታውያን፥ ሡካታውያን ነበሩ፤ እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የወጡ ቄናውያን ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በያቤጽ የሚኖሩ የጸሐፍት ጐሣዎች ቲርዓውያን፣ ሺምዓታውያን፣ ሡካታውያን። እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የመጡ ቄናውያን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በያቤጽም የተቀመጡ የጸሐፊዎች ወገኖች፤ ቲርዓውያን፥ ሺምዓታውያን፥ ሡካታውያን ነበሩ፤ እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የወጡ ቄናውያን ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቲርዓውያን፥ ሺምዓውያንና ሱካውያን የተባሉት ታሪክ በመጻፍና በመገልበጥ ጥበበኞች የነበሩት ጐሣዎች ያዕቤጽ ተብላ በምትጠራ ትንሽ ከተማ ይኖሩ ነበር፤ እነርሱም ከሬካባውያን አባት ከሐሜት የወጡ ቄናውያን ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በያቤጽም የተቀመጡ የጸሐፊዎች ወገኖች፤ ቲርዓውያን፥ ሺምዓታውያን፥ ሡካታውያን ነበሩ፤ እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የወጡ ቄናውያን ናቸው። |
ከዚያም በሄደ ጊዜ የሬካብን ልጅ ኢዮናዳብን በመንገድ አገኘው፤ ተቀብሎም መረቀው፤ ኢዩም፥ “ልቤ ከልብህ ጋር ቅን እንደ ሆነ ያህል ልብህ ከልቤ ጋር በቅንነት ነውን?” አለው። ኢዮናዳብም፥ “አዎን” አለው። ኢዩም፥ “እውነትህስ ከሆነ እጅህን ስጠኝ” አለ። እጁንም ሰጠው፤ ወደ እርሱም ወደ ሰረገላው አወጣው።
በኬብሮን ለዳዊት የተወለዱለት ልጆች እነዚህ ናቸው። በኵሩ አምኖን ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆም፥ ሁለተኛውም ዶለህያ ከቀርሜሎሳዊቱ ከአቢግያ፥
ይህም ዕዝራ ከባቢሎን ወጣ፤ እርሱም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ሕግ ዐዋቂ ነበረ፤ የአምላኩም የእግዚአብሔር እጅ በእርሱ ላይ ነበረችና ንጉሡ ያሻውን ሁሉ ሰጠው።
ስለዚህ በፊቴ የሚቆም ሰው ከሬካብ ልጅ ከኢዮናዳብ ወገን ለዘለዓለም አይታጣም፥” ይላል የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
“እናንተስ፦ ጥበበኞች ነን የእግዚአብሔርም ሕግ ከእኛ ጋር ነው እንዴት ትላላችሁ? እነሆ ጸሓፊዎቻቸውም ከንቱ ሆኑ፤ በሐሰትም ብርዕ ተጠቀሙ።
የቄናዊው የሙሴ አማት የዮባብ ልጆችም ከዘንባባ ከተማ ተነሥተው ከዓራድ በአዜብ በኩል ወዳለው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ ወደ ይሁዳ ልጆች ሄደው ከሕዝቡ ጋር ተቀመጡ።
ቄናዊውም ሔቤር ከሙሴ አማት ከኢዮባብ ልጆች ከቄናውያን ተለይቶ ድንኳኑን በቃዴስ አጠገብ እስከ ነበረው ታላቅ ዛፍ ድረስ ተከለ።
ሳኦልም ቄኔዎናውያንን፥ “ከእነርሱ ጋር እንዳላጠፋችሁ ከአማሌቃውያን መካከል ተነሥታችሁ ሂዱ፤ ከግብፅ በወጡ ጊዜ ለእስራኤል ልጆች ቸርነት አድርጋችኋልና” አላቸው። ቄኔዎናውያንም ከአማሌቃውያን መካከል ወጡ።