“ሮቤል እርሱ የበኵር ልጄና ኀይሌ፥ የልጆችም መጀመሪያ ነው፤ ክፉ ሆነ፤ አንገቱንም አደነደነ። ጭንቅ ነገርንም አደረገ።
1 ዜና መዋዕል 2:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢያሬምሄል ወንድም የካሌብ ልጆች በኵር የዚፍ አባት ማሪስ ነው፤ የኬብሮንም አባት የማሪስ ልጆች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይረሕምኤል ወንድም የካሌብ ወንዶች ልጆች፤ የበኵር ልጁ ሞሳ ሲሆን፣ እርሱም ዚፍን ወለደ፤ ዚፍም መሪሳን ወለደ፤ መሪሳም ኬብሮንን ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይረሕምኤልም ወንድም የካሌብ ልጆች በኩሩ የዚፍ አባት ሞሳ፥ የኬብሮንም አባት የመሪሳ ልጆች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይራሕመኤል ወንድም የነበረው የካሌብ በኲር ልጅ ስሙ ሜሻዕ ይባል ነበር፤ ይህም ሜሻዕ ዚፍ ተብሎ የሚጠራውን ወንድ ልጅ ወለደ፤ ዚፍም ማሬሻን ወለደ፤ ማሬሻም ኬብሮንን ወለደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይረሕምኤልም ወንድም የካሌብ ልጆች በኵሩ የዚፍ አባት ሞሳ፥ የኬብሮንም አባት የመሪሳ ልጆች ነበሩ። |
“ሮቤል እርሱ የበኵር ልጄና ኀይሌ፥ የልጆችም መጀመሪያ ነው፤ ክፉ ሆነ፤ አንገቱንም አደነደነ። ጭንቅ ነገርንም አደረገ።
ደግሞም የምድሜናን አባት ስጋብን የመክቢናንና የጌባልን አባት ሳዑልን ወለደች፤ የካሌብም ሴት ልጅ አስካ ነበረች።
ልጁ በብዙዎች ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ አስቀድሞ ያወቃቸውንና የመረጣቸውን እነርሱን ልጁን ይመስሉ ዘንድ አዘጋጅቶአቸዋል።
ስማቸው በሰማይ ወደ ተጻፈ ወደ ማኅበረ በኵርም፥ ሁሉን ወደሚገዛም ወደ እግዚአብሔር፥ ወደ ፍጹማን ጻድቃንም ነፍሳት፥
የዚፍ ሰዎችም ከአውክሞዲስ ወደ ሳኦል ወደ ኮረብታው ወጥተው እንዲህ አሉት፥ “እነሆ፥ ዳዊት በየሴሞን ቀኝ በጠባቡ በኩል በኤኬላ ኮረብታ ላይ በቄኒ ውስጥ በማሴሬት በእኛ ዘንድ ተሸሽጎ የለምን?
የዚፍ ሰዎችም ከአውክሞዲስ ወደ ኮረብታው ወደ ሳኦል መጥተው፥ “እነሆ፥ ዳዊት በየሴሞን ፊት ለፊት ባለው በኤኬላ ኮረብታ ላይ ከእኛ ጋር ተሸሽጎ አለ” አሉት።