መዝሙር 4:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙዎች፣ “አንዳች በጎ ነገር ማን ያሳየናል?” ይላሉ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የፊትህ ብርሃን በላያችን ይብራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጽድቅን መሥዋዕት ሠዉ፥ በጌታም ታመኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “መልካሙን ነገር ማን ያሳየናል?” የሚሉ ብዙዎች ናቸው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ሆይ! የፊትህ ብርሃን በእኛ ላይ ይብራ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በጎውን ማን ያሳየናል?” የሚሉ ብዙዎች ናቸው። አቤቱ፥ የፊትህ ብርሃን በላያችን ታወቀ። |
ምድሪቱን የወረሱት በሰይፋቸው አልነበረም፤ ድልንም የተጐናጸፉት በክንዳቸው አይደለም፤ አንተ ወድደሃቸዋልና ቀኝ እጅህ፣ ክንድህና የፊትህ ብርሃን ይህን አደረገ።
ገንዘባችሁን እንጀራ ባልሆነ ነገር ላይ ለምን ታጠፋላችሁ? በማያጠግብስ ነገር ላይ ለምን ጕልበታችሁን ትጨርሳላችሁ? ስሙ፤ እኔን ስሙኝ፤ መልካም የሆነውንም ብሉ፤ ነፍሳችሁም በጥሩ ምግብ ትደሰታለች።
ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያነጻ ሰው ይቀመጣል፤ ሌዋውያንንም አንጽቶ እንደ ወርቅና እንደ ብር ያጠራቸዋል፤ ከዚያም እግዚአብሔር ቍርባንን በጽድቅ የሚያቀርቡ ሰዎች ይኖሩታል፤
አሕዛብን ወደ ተራራው ይጠራሉ፤ በዚያም የጽድቅን መሥዋዕት ያቀርባሉ። በባሕሮች ውስጥ ያለውን በተትረፈረፈ ብልጽግና፣ በአሸዋውም ውስጥ የተደበቀውን ሀብት ይደሰቱበታል።”
እናንተ፣ “ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህች ወይም ወደዚያች ከተማ እንሄዳለን፤ በርሷም አንድ ዓመት እንቈያለን፤ እንነግዳለን፤ እናተርፋለንም” የምትሉ እንግዲህ ስሙ።