መዝሙር 20:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የልብህን መሻት ይስጥህ፤ ዕቅድህን ሁሉ ያከናውንልህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መባዎችህን ሁሉ ያስብልህ፥ የሚቃጠል መሥዋዕትህን ያለምልምልህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የልብህን ምኞት ይስጥህ፤ ሐሳብህን ሁሉ ይፈጽምልህ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕይወትን ለመነህ፥ ሰጠኸውም፥ ለረዥም ዘመን ለዘለዓለሙ። |
ንጉሥ ሰሎሞን ለሳባ ንግሥት የፈለገችውንና የጠየቀችውን ሁሉ ሰጣት፤ ስጦታውም እርሷ ካመጣችለት በላይ ነበር። ከዚያም ከአጃቢዎቿ ጋራ ወደ አገሯ ተመለሰች።
ሚስቱ ግን መልሳ እንዲህ አለችው፣ “እግዚአብሔር ሊገድለን ቢፈልግ ኖሮ፣ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህል ቍርባኑን ከእጃችን ባልተቀበለን፤ ደግሞም ይህን ነገር ሁሉ ባላሳየንና እንዲህ ያለውንም ነገር በዚህ ጊዜ ባልነገረን ነበር።”
አሁንም ንጉሥ ጌታዬ የባሪያውን ቃል ያድምጥ፤ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አነሣሥቶህ እንደ ሆነ፣ ቍርባን ይቀበል፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ሰዎች ከሆኑ፣ በእግዚአብሔር ፊት የተረገሙ ይሁኑ፤ ‘ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ’ ብለው በእግዚአብሔር ርስት ድርሻ እንዳይኖረኝ ዛሬ አሳድደውኛልና።