ዘኍል 33:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሬሞን ዘፋሬስ ተነሥተው በልብና ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሬሞን ዘፋሬስም ተጉዘው በልብና ሰፈሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሪሞንፔሬዝ ተነሥተው በመጓዝ በሊብና ሰፈሩ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሬሞት ዘፋሬስም ተጕዘው በልብና ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሬሞን ዘፋሬስም ተጕዘው በልብና ሰፈሩ። |
ሙሴም የቤተ መቅደሱን ንዋየ ቅድሳትና ምልክት መስጫ የሆኑትን መለከቶች ከያዘው ከካህኑ ከአልዓዛር ልጅ ከፊንሐስ ጋራ ከየነገዱ አንዳንድ ሺሕ ሰው ለጦርነት ላከ።
ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ዓረባ በተባለው ምድረ በዳ ከሱጵ ትይዩ፣ በፋራንና በጦፌል፣ በላባን፣ በሐጼሮትና በዲዛሃብ መካከል ሳሉ፣ ሙሴ ለእስራኤል ሁሉ የተናገረው ቃል ይህ ነው።