La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 17:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን ደን የለበሰው ኰረብታማው አገር የእናንተ ነው፤ ሄዳችሁ መንጥሩት፣ ዳር ድንበሩ ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ከነዓናውያን የብረት ሠረገላ ቢኖራቸውና ብርቱዎች ቢሆኑም እንኳ ከዚያ ታስወጧቸዋላችሁ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን ተራራማው አገር ለአንተ ይሆናል፥ ዱር እንኳን ቢሆንም ትመነጥረዋለህ፥ ለአንተም ይሆናል፤ ለከነዓናውያንም የብረት ሰረገሎች ቢኖሩአቸው የበረቱም ቢሆኑ ታሳድዳቸዋለህ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ኮረብታማው አገር የእናንተ ይሆናል፤ ጫካም ቢሆን መንጥራችሁ ዳር እስከ ዳር የራሳችሁ ርስት አድርጉት፤ ስለ ከነዓናውያን ጉዳይ የሆነ እንደሆን ምንም የብረት ሠረገሎች ቢኖራቸውና ምንም ብርቱዎች ቢሆኑ ነቃቅላችሁ ልታባርሩአቸው ትችላላችሁ።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነገር ግን ተራ​ራ​ማው ሀገር ለእ​ና​ንተ ይሆ​ናል፤ ዱር እንኳ ቢሆ​ንም ትመ​ነ​ጥ​ሩ​ታ​ላ​ችሁ፤ ለእ​ና​ን​ተም ይሆ​ናል፤ ለከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም የተ​መ​ረጡ ፈረ​ሶ​ችና የብ​ረት ሰረ​ገ​ሎች ቢሆ​ኑ​ላ​ቸው፥ የበ​ረቱ ቢሆ​ኑም እና​ንተ እስ​ክ​ታ​ጠ​ፉ​አ​ቸው ድረስ ትበ​ረ​ቱ​ባ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን ተራራማው አገር ለአንተ ይሆናል፥ ዱር እንኳን ቢሆንም ትመነጥረዋለህ፥ ለአንተም ይሆናል፥ ለከነዓናውያንም የብረት ሰረገሎች ቢሆኑላቸው የበረቱም ቢሆኑ ታሳድዳቸዋለህ አላቸው።

Ver Capítulo



ኢያሱ 17:18
18 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን በያዕቆብ ኀያል አምላክ ክንድ፣ እረኛው በሆነው በእስራኤል ዐለት፣ ቀስቱ ጸና፤ ጠንካራ ክንዱም ቀለጠፈ።


ሰራዊቱ እስራኤልን ለመውጋት ተሰልፎ ወደ ሜዳ ወጣ፤ ጦርነቱም በኤፍሬም ደን ውስጥ ሆነ።


ታዲያ ለዚህ ምን እንመልሳለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ከሆነ፣ ማን ሊቃወመን ይችላል?


ምንም አይለየንም፤ በዚህ ሁሉ በወደደን በርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።


በግርማው እንደ በኵር ኰርማ ነው፤ ቀንዶቹም የጐሽ ቀንዶች ናቸው። በእነርሱም ሕዝቦችን፣ በምድር ዳርቻ ላይ ያሉትን እንኳ ሳይቀር ይወጋል፤ እነርሱም የኤፍሬም ዐሥር ሺሕዎቹ ናቸው፤ የምናሴም ሺሕዎቹ እንደዚሁ ናቸው።”


ስለዚህ በሙሉ ልብ፣ “ጌታ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” እንላለን።


“ከሊባኖስ እስከ ማስሮን ባለው ተራራማ ምድር ላይ የሚኖሩትን ሁሉ፣ ሲዶናውያንንም ጭምር እኔው ራሴ ከእስራኤላውያን ፊት አሳድጄ አስወጣቸዋለሁ። ብቻ አንተ ባዘዝሁህ መሠረት ምድሪቱን ርስት አድርገህ ለእስራኤላውያን አካፍል።


ከዚያም በመቀጠል ከተራራው ዐናት ተነሥቶ ወደ ኔፍቶ ምንጮች በማምራት፣ በዔፍሮን ተራራ ላይ ያሉትን ከተሞች ዐልፎ ይወጣና ቂርያትይዓይሪም ተብሎ ወደሚጠራው ወደ በኣላ ቍልቍል ይወርዳል።


ኢያሱ ግን ለዮሴፍ ዘሮች ለኤፍሬምና ለምናሴ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ ቍጥራችሁ ብዙ፣ እጅግም ኀያል እንደ መሆናችሁ ድርሻችሁ አንድ ብቻ አይሆንም፤


ስለዚህም በኰረብታማው በንፍታሌም ምድር በገሊላ ቃዴስን፣ በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር ሴኬምን፣ በኰረብታማው በይሁዳ ምድር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያት አርባቅን ለዩ።


በተራራማው በኤፍሬም አገር በአርማቴም መሴፋ የሚኖር ሕልቃና የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም ኤፍሬማዊ ሲሆን፣ የኤያሬምኤል ልጅ፣ የኢሊዩ ልጅ፣ የቶሑ ልጅ፣ የናሲብ ልጅ፣ ነበረ።