ኢያሱ 16:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድንበሩ አሁንም ከታጱዋ በምዕራብ በኩል አድርጎ ወደ ቃና ወንዝ ይወርድና ከባሕሩ ላይ ይቆማል። እንግዲህ የኤፍሬም ነገድ በየጐሣ በየጐሣቸው የተካፈሉት ርስት ይህ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበሩም ከታጱዋ ወደ ምዕራብ እስከ ቃና ወንዝ ድረስ አለፈ፥ መጨረሻውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። የኤፍሬም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይኸው ድንበር በምዕራብ በኩል ከታፑሐ ተነሥቶ እስከ ቃና ወንዝ ይደርስና መጨረሻው የሜድትራኒያን ባሕር ይሆናል፤ ለኤፍሬም ነገድ በየወገኑ ርስት ሆኖ የተሰጠው ምድር ይህ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንበሩም ከጣፉ ወደ ባሕር እስከ ኬልቃን ወንዝ ድረስ ያልፋል፥ መውጫውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። የኤፍሬም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንበሩም ከታጱዋ ወደ ምዕራብ እስከ ቃና ወንዝ ድረስ አለፈ፥ መውጫውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። የኤፍሬም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ። |
ምድራቸውና መኖሪያቸው ቤቴልንና በዙሪያዋ የሚገኙትን ከተሞች፣ በስተምሥራቅ ነዓራን፣ በስተ ምዕራብ ጌዝርንና መንደሮቿን፣ እንዲሁም ሴኬምንና መንደሮቿን፣ ከዚያም ዐልፎ ጋያንና መንደሮቿን በሙሉ ያጠቃልል ነበር።
የምናሴ ርስት ከአሴር አንሥቶ ከሴኬም በስተምሥራቅ እስካለችው እስከ ሚክምታት ይደርሳል፤ ድንበሩም ወደ ደቡብ በመዝለቅ በዓይንታጱዋ የሚኖረውን ሕዝብ ይጨምራል።