ኤርምያስ 9:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ተራሮች አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይ እላለሁ፤ በምድረ በዳ ስላሉትም መሰማሪያዎች ዐዝናለሁ። ሰው የማያልፍባቸው ባድማ ሆነዋል፤ የከብቶች ጩኸት አይሰማም፤ የሰማይ ወፎች ሸሽተዋል፤ የዱር አራዊትም ጠፍተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለተራሮች ልቅሶንና እንጉርጉሮን ለምድረ በዳ ማሰማርያዎችም ዋይታን አነሣለሁ፥ ሰው እንዳያልፍባቸው ባድማ ሆነዋልና። ሰዎችም የከብቱን ድምፅ አይሰሙም፤ ከሰማይ ወፎች ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሸሽተው ሄደዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ሁሉም ወና ስለ ሆኑና በእነርሱም ላይ የሚዘዋወርባቸው ስለሌለ፥ ስለ ተራራዎች አዝናለሁ፤ ስለ ሜዳዎችም አለቅሳለሁ፤ የከብቶች ድምፅ ዳግመኛ አይሰማም፤ የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊት ሁሉ ሸሽተው ጠፍተዋል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተራሮቹ ላይ አልቅሱ፤ በምድረ በዳም ጎዳና ላይ እዘኑ፤ ሰው ጠፍትዋልና፤ የሚመላለስም የለምና ሙሾውንም አሙሹ፤ የሰማይ ወፍ ድምፅንም እስከ ከብት ድምፅ ድረስ አይሰሙም፤ ደንግጠውም ተማርከው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለተራሮች ልቅሶን ለምድረ በዳ ማሰማርያዎችም ዋይታን አነሣለሁ፥ ሰው እንዳያልፍባቸው በእሳት ተቃጥለዋልና። ሰዎችም የከብቱን ድምፅ አይሰሙም፥ ከሰማይ ወፎች ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሸሽተው ሄደዋል። |
ምድሪቱ በዝናብ ዕጦት የምትጐዳው፣ የሜዳውም ሣር ሁሉ በድርቅ የሚመታው እስከ መቼ ነው? ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ፣ እንስሳትና አዕዋፍ ጠፍተዋል፤ ደግሞም ሕዝቡ፣ “በእኛ ላይ የሚሆነውን አያይም” ብለዋል።
እነርሱም፣ ‘ከግብጽ ምድር ያወጣን፣ በወና ምድረ በዳ፣ በጐድጓዳና በበረሓ መሬት፣ በደረቅና በጨለማ ቦታ፣ ሰው በማያልፍበትና በማይኖርበት ስፍራ የመራን እግዚአብሔር ወዴት ነው?’ ብለው አልጠየቁም።
ምድሪቱ በአመንዝሮች ተሞልታለች፤ ከርግማን የተነሣ ምድሪቱ ታለቅሳለች፤ በምድረ በዳ ያሉት መሰማሪያዎች ደርቀዋል። ነቢያቱም ጠማማ መንገድ ተከትለዋል፤ ሥልጣናቸውን ያለ አግባብ ተጠቅመዋል።
“ ‘እግዚአብሔር ቍጣው የወረደበትን ይህን ትውልድ ስለ ናቀውና ስለ ተወው፣ ጠጕርሽን ቈርጠሽ ጣዪ፤ በባድሞቹ ኰረብቶች ላይ ሆነሽም ሙሾ አውጪ።
“የማለቅሰው ስለ እነዚህ ነገሮች ነው፤ ዐይኖቼ በእንባ ተሞልተዋል፣ ሊያጽናናኝ የቀረበ፣ መንፈሴንም ሊያረጋጋ የሞከረ ማንም የለም፤ ጠላት በርትቷልና ልጆቼ ተጨንቀዋል።”
ዐይኔ በልቅሶ ደከመ፤ ነፍሴ በውስጤ ተሠቃየች፤ ልቤም በሐዘን ፈሰሰች፣ በከተማዪቱ መንገዶች ላይ፣ ሕዝቤ ተደምስሰዋልና፤ ልጆችና ሕፃናት ደክመዋልና።
“የዱር አራዊትንም በአገሪቱ ላይ ሰድጄ፣ አገሪቱን ሕፃናት አልባ ቢያደርጓትና ከአራዊቱም የተነሣ ምድሪቱ ሰው እስከማያልፍባት ባድማ ብትሆን፣
መሠዊያዎቻችሁ እንዲፈራርሱና እንዲወድሙ፣ ጣዖቶቻችሁ እንዲሰባበሩና እንዲደቅቁ፣ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁ እንዲንኰታኰቱ፣ የእጆቻችሁም ሥራ እንዲደመሰስ፣ የምትኖሩባቸው ከተሞች ሁሉ ባድማ ይሆናሉ፤ ማምለኪያ ኰረብቶችም እንዳልነበሩ ይሆናሉ።
ካህናት ሆይ፤ ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ፤ እናንተ በመሠዊያው ፊት የምታገለግሉ፣ ዋይ በሉ፤ እናንተ በአምላኬ ፊት የምታገለግሉ፣ ኑ፤ ማቅ ለብሳችሁ ዕደሩ፤ የእህል ቍርባኑና የመጠጥ ቍርባኑ፣ ከአምላካችሁ ቤት ተቋርጧልና።
ስለዚህ ጌታ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በየመንገዱ ሁሉ ወየው ተብሎ ይለቀሳል፤ በአደባባዩም የሥቃይ ጩኸት ይሆናል፤ ገበሬዎች ለልቅሶ፣ አልቃሾችም ለዋይታ ይጠራሉ።
በዚያ ቀን ሰዎች ይሣለቁባችኋል፤ በሐዘን እንጕርጕሮ እንዲህ እያሉ ያፌዙባችኋል፤ ‘እኛ ፈጽሞ ጠፍተናል፤ የወገኔ ርስት ተከፋፍሏል። ከእኔ ነጥቆ ወስዶ፣ ዕርሻዎቻችንን ላሸነፉን አከፋፈለ።’ ”
ስለዚህ በእናንተ ምክንያት፣ ጽዮን እንደ ዕርሻ ትታረሳለች፣ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ የቤተ መቅደሱም ኰረብታ ዳዋ የወረሰው ጕብታ ይሆናል።