ኤርምያስ 14:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትንቢቱ የተነገረለትም ሕዝብ ከሰይፍና ከራብ የተነሣ በኢየሩሳሌም አደባባዮች ይወድቃል፤ እነርሱንም ሆነ ሚስቶቻቸውን ወይም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን የሚቀብራቸው አይገኝም። ለበደላቸው የሚገባውንም ቅጣት በላያቸው አወርዳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትንቢት የሚናገሩላቸውም ሰዎች ከራብና ከሰይፍ የተነሣ በኢየሩሳሌም አደባባይ ይጣላሉ፤እነርሱንና ሚስቶቻቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም የሚቀብራቸው አይገኝም፤ ክፋታቸውንም በእነርሱ ላይ አወርድባቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም የተነበዩላቸው ሕዝብ ሁሉ በራብና በጦርነት ይሞታሉ፤ ሬሳቸውም ሁሉ በኢየሩሳሌም ውስጥ በየመንገዱ ይወድቃል፤ የሚቀብራቸውም አይኖርም፤ ይህም በሚስቶቻቸው፥ በወንዶች ልጆቻቸውና በሴቶች ልጆቻቸው ሳይቀር በሁሉም ላይ ይፈጸማል፤ በበደላቸውም መጠን ተገቢ ቅጣታቸውን እሰጣቸዋለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትንቢት የሚናገሩላቸውም ሰዎች ከራብና ከሰይፍ የተነሣ በኢየሩሳሌም መንገዶች ይበተናሉ፤ ክፋታቸውንም አፈስስባቸዋለሁና እነርሱንና ሚስቶቻቸውን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም የሚቀብራቸው አይገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትንቢት የሚናገሩላቸውም ሰዎች ከራብና ከሰይፍ የተነሣ በኢየሩሳሌም አደባባይ ይበተናሉ፥ ክፋታቸውንም አፈስስባቸዋለሁ እነርሱንና ሚስቶቻቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም የሚቀብራቸው አይገኝም። |
ወንዶች ልጆችሽ ዝለዋል፤ በወጥመድ እንደ ተያዘ ሚዳቋ፣ በየጐዳናው አደባባይ ላይ ተኝተዋል። የእግዚአብሔር ቍጣ፣ የአምላክሽም ተግሣጽ ሞልቶባቸዋል።
“በአደገኛ በሽታ ይሞታሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ አይቀበሩም፤ በምድርም ላይ እንደ ጕድፍ ይጣላሉ። በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።”
ስለዚህ ልጆቻቸውን ለራብ፣ ለሰይፍም ስለት አሳልፈህ ስጥ፤ ሚስቶቻቸው የወላድ መካን፣ መበለትም ይሁኑ፤ ወንዶቻቸው በሞት ይቀሠፉ፤ ጕልማሶቻቸው በጦር ሜዳ ለሰይፍ ይዳረጉ።
ጳስኮር ሆይ፤ አንተና በቤትህ የሚኖሩት ሁሉ ወደ ባቢሎን ትጋዛላችሁ። አንተና በሐሰት ትንቢት የተነበይህላቸው ወዳጆችህ በዚያ ትሞታላችሁ፤ በዚያም ትቀበራላችሁ።’ ”
‘እኔ አልላክኋቸውም’ ይላል እግዚአብሔር ‘የሐሰት ትንቢት በስሜ ይናገራሉ፤ ስለዚህ እናንተንና ትንቢት የሚናገሩላችሁን ነቢያት አሳድዳለሁ፤ እናንተም ትጠፋላችሁ።’ ”
ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናት በነቢያቱ ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ይወድዳሉ፤ ፍጻሜው ሲደርስ ግን ምን ታደርጉ ይሆን?”
“ ‘በዚያ ጊዜ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ የይሁዳ ነገሥታትና መኳንንት ዐፅም፣ የካህናትና የነቢያት ዐፅም፣ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ዐፅም ከየመቃብራቸው ይወጣል።
በወደዷቸውና በአገለገሏቸው እንዲሁም በተከተሏቸው፣ ባማከሯቸውና ባመለኳቸው በፀሓይ፣ በጨረቃና በሰማያት ከዋክብት ሁሉ ፊት ይሰጣል፤ አይሰበሰብም ወይም አይቀበርም፤ ነገር ግን እንደ ተጣለ ጕድፍ በምድር ላይ ይበተናል።
እናንተ ሴቶች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ጆሮቻችሁን ከአንደበቱ ለሚወጡት ቃላት ክፈቱ፤ ሴቶች ልጆቻችሁን ዋይታ፣ አንዳችሁም ሌላውን ሙሾ አስተምሩ።
እንዲህ በሉ፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘የሰዎች ሬሳ፣ በሜዳ እንደ ተጣለ ጕድፍ፣ ማንም እንደማይሰበስበው፣ ከዐጫጅ ኋላ እንደ ተተወ ቃርሚያ ይወድቃል።’ ”
“ ‘ሰዎች ምድሪቱን ለማጽዳት በየጊዜው ይቀጠራሉ። አንዳንዶቹ ምድሪቱን ያሥሣሉ፤ ከእነርሱም በተጨማሪ ሌሎች ሳይቀበሩ የቀሩትን ይቀብራሉ። ከሰባት ወር በኋላም ፍለጋ ይጀምራሉ።
“ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ሚስትህ በከተማዪቱ ውስጥ ጋለሞታ ትሆናለች፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ምድርህም በገመድ እየተለካ ይከፋፈላል፤ አንተ ራስህ በረከሰ ምድር ትሞታለህ፤ እስራኤልም ከትውልድ አገሩ፣ ተማርኮ ይሄዳል።’ ”